SuperBootsUp

Edit Content

እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ?

ድህረገፅ ዲዛይን

ድህረገጾን አሁን ያግኙ

የፌስቡክ ማስታወቂያዎች

ንግድዎን በፌስቡክ ያሳድጉ

ላንዲንግ ፔጅ

የንግድ ላንዲንግ ፔጅ ያግኙ

SEO

#1 የጉግል ፍለጋ ደረጃ ያግኙ

ጎግል ማስተዋወቂያ

በጎግል ማስታወቂያ ሽያጭዎን ያሳድጉ

የቪዲዮ ፕሮዳክሽን ስራ

ከፍተኛውን የጥራት ደረጃ ተጎናጸፉ የቪዲዮ ማስታወቂያዎች እና ትክክለኛው የማስተዋወቅ ቴክኒክ

ሞዴል እና ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ማስተዋወቅ

ለሞዴሎች እና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ማስተዋወቅ

የኩባንያ ብራንዲንግ፣የአርማ(ሎጎ) ንድፍ (ዲዛይን)

የዲጂታል ግብይት ተሳትፎዎን ከእኛ ጋር ይለኩሱ

የድርጅቶች እና የግለሰቦች ሥልጠና

የድርጅት ሥልጠናና ዕድገት ላይ ኢንቨስት ያድርጉ

ሶፍትዌር ማበልጸግ እና አይቲ መፍትሄዎች

ምርጥ ሶፍትዌር እና የአይቲ መፍትሄዎችን ያግኙ

የስኬታማ ሽያጭ ጥበብ ሚስጥራት መጽሐፍ

ማናቸውንም ነገር ለማንኛውም ሰው መሸጥ የመቻልን ጥበብ ይካኑ!!

ሱፐር ቡስት አፕ የ ሶፍትዌር እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎቶች

የእኛ አገልግሎቶች

ድርጅታችን ሱፐር ቡስት አፕ የሚሰኝ ሲሆን፣ ከዲጂታል ግብይት እስከ ሶፍትዌርና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (አይ.ቲ) ሥራዎች ድረስ አገልግሎቶችን በስፋት እናቀርባለን፡፡ ኩባንያዎች ዲጂታል መሣሪያዎችን በመጠቀም ሥራቸውን እንዲሠሩ የማብቃት እና በዚህ ዲጂታል ዓለም ውስጥ አሸናፊ የሚሆኑበትን መሣሪያ እና መንገድ የማቅረብ ሥራዎችን እንሠራለን፡፡ አገራችን ሥራዎች በዲጂታል መንገድ ወደ ሚሠሩበት ደረጃ ለመድረስ በምታደርገው ጉዞ የበኩላችንን አሻራ ለማሳረፍ ያለ እረፍት በትጋት እየሠራን እንገኛለን፡፡ በዘመናዊነት ቀዳሚና ውጤታማ የሆኑትን የሶፍትዌርና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሥራዎች በማቅረብ አንድ እርምጃ ወደፊት ተራምደው ቀዳሚ እንዲሆኑ ልናግዝዎ ተዘጋጅተናል፡፡    

ሱፐር ቡስት አፕ፣ ድርጅትዎ ውጤታማ ሥራዎችን እንዲሠራና ምርታማ እንዲሆን የሚያስችሉትን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ሥራዎችን በመሥራት ወደ ፊት ለመራመድ በሚያደርጉት ጥረት ታላቅ ድጋፍ የሚያደርግልዎ ዓይነተኛ አጋርዎ ነው፡፡ የሱፐር ቡስት አፕ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ የሥራዎን ጥራት ደረጃ ለማስጠበቅ፣ ያለ ብዙ የሰው ጣልቃ ገብነት ሥራዎችን ለመሥራት (automating) እንዲሁም የሥራ እንቅስቃሴዎን እና የሃብት ፍሰትዎን ለማፋጠን የሚያግዙ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያላቸውን አገልግሎቶች ለእርስዎ በማቅረብ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡

ምስክርነቶች

ደንበኞች ስለ እኛ የሚሉት

ምስክርነቶች

ደንበኞች ስለ እኛ የሚሉት

የምናቀርባቸው የሶፍትዌርና የኢንፎርሜሽ ቴክኖሎጂ ውጤቶች የሚከተሉትን ሥራዎች ያካትታሉ፡፡

 • የድርጅት ሃብት ዕቅድ (Enterprise Resource Planning – ERP)
 • የትምህርት ቤት አስተዳደር ሥርዓት( School Management System)
 • መተግበሪያ ልማት (App Development)

የድርጅት ሃብት አስተዳደር (ኢ.አር.ፒ)

ኢ. አር. ፒ፣ ያለ ብዙ የባለሙያ ጣልቃ ገብነት ሥራዎችን መሥራት የሚችል (automation) እንዲሁም፣ የፋይናንስ፣ የሰው ሃብት አስተዳደር፣ የአምራችነት፣ የአቅርቦት ሰንሰለት፣ የአገልግሎቶች ሰጪነት፣ የግዢ እና ሌሎች ሥራዎችን መሥራት የሚችል አቅም በውስጡ የያዘና አጠቃላይ ድርጅትዎን ለማስተዳደር የሚረዳዎ የሶፍትዌር ሥርዓት ነው፡፡

ኢ.አር.ፒ፣ በድርጅት ውስጥ ያሉ አጠቃላይ ሃብቶችንና አጠቃቀማቸውን በተቀናጀ ሁኔታ የማስተዳደር ሂደት ነው፡፡ የተለመዱ የንግድ ሥራ እንቅስቃሴዎችን የሚያከናውኑ የንግድ ሥራ መተግበሪያዎች ወይም መመሪያዎች ስብስብ ነው፡፡ አገልግሎቶችን በማሻሻል፣ በመከታተል እና በማስቀጠል የንግድ ሥራን የሚደግፍ ነው፡፡

ኢ.አር.ፒን ለምን እንጠቀማለን?

የሱፐር ቡስት አፕ ኢ. አር. ፒ መመሪያዎች ወይም ባሕርያት

የሰው ሃብት አስተዳደር መመሪያ አብዛኛውን ጊዜ ሁሉንም የሰው ሃብት አስተዳደር መተግበሪያ ባሕርያትን እና ሌሎች ተጨማሪ ዝርዝር ሥራዎችን የያዘ መመሪያ ነው፡፡ በሠራተኞች ዘንድ የሰው ሃብት አስተዳደር (HRM) እንደ ደንበኞች ግንኙነት አስተዳደር (CRM) ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ይህ በብዙ ሰዎች የሚታወቀው መመሪያ ዝርዝር መረጃዎችን የሚይዝ ሲሆን፣ የአፈጻጸም ግምገማዎችን፣ የሥራ ኃላፊነት ዝርዝሮችን እና የቅጥር ደብዳቤዎችን የመሣሠሉ ሰነዶችንም ያቀፈ ነው፡፡ ሥራ የተሠራባቸውን ሰዓታት ብቻ ሳይሆን፣ የሚከፈልባቸውን የእረፍት ሰዓታት፣ በህመም ምክንያት የሚመዘገቡ ቀሪዎችን፣ እንዲሁም የጥቅማ ጥቅም ዝርዝሮችንም ይይዛል፡፡

የፋይንስና የሂሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያው፣ ከሁሉም የበለጠ አስፈላጊው የኢ. አር. ፒ መመሪያ ነው፤ ምክንያቱም የንግድ ሥራ ድርጅቶች ያሉበትን አሁናዊ እና የወደፊት የፋይናንስ ሁኔታቸውን እንዲገነዘቡ ያደርጋቸዋል፡፡ የዚህ መመሪያ ዋነኛ መለያ ባሕርያት፣ ለሌላ አካል ሊከፈሉ የሚገባቸውን (AP) እና ተሰብሳቢ (ከሌላ ወገን የሚሰበሰቡ/ለድርጅቱ የሚከፈሉ) (AR) ክፍያዎችን፣ እንዲሁም አጠቃላዩን የሒሳብ ሰነድ ሁኔታ መከታተል ናቸው፡፡ የሂሳብ ሰነዶችን (ባላንስ ሽት)፣ ደረሰኞችን እና የግብር ክፍያዎችን የመሣሠሉ በጣም ጠቃሚ ሥራዎች ያዘጋጃል፤ ሥራዎቹንም በውስጡ ያከማቻል፡፡

የመጋዘን አስተዳደር ሥርዓት (warehouse management system (WMS))፣ ድርጅቶች፣ ዕቃዎች ወደ መጋዘን ከገቡበት ጊዜ አንሥቶ እስከሚወጡበት ጊዜ ድረስ መቆጣጠርና ማስተዳደር እንዲችሉ የሚያደርጓቸውን ሶፍትዌርና ሂደቶችን የያዘ ነው፡፡.

የበጀት አስተዳደር፣ የበጀትዎን ፍሰት አጀማመር ሂደትን እንዲያውቁት እና የሥጋትን (risk)፣ የንግድ ሥራ አቅጣጫን፣ አቅምን እንዲሁም የበጀት እጥረትን ከግምት ያስገባ ምልከታ እንዲኖርዎት ያደርጋል፡፡ በዓመታት ውስጥ የሚኖሩትን ለውጦች በማስተናገድ፣ የበጀት መዋቅሩን ዓመታዊ ዕቅድ የሚያሻሽል የ”ቢሆንስ” ምልከታን (a what-if scenario) ያዘጋጃል/ ይፈጥራል፡፡ በተጨማሪም፣ ዓመታዊ በጀትን ለማቀድ የሚያገለግል መዋቅርን ይፈጥራል፣ የበጀት ጥያቄዎችን ያስናግዳል፣ ዓመታዊ ዕቅድ ማጠቃለያን ያቀርባል፣ የ”ቢሆንስ” ምልከታዎችን ያዘጋጃል እንዲሁም በበጀት መዝጊያ ላይ የሚሠሩ ሥራዎችን ይሠራል፡፡

የደንበኞች ግንኙነት አስተዳደር (customer relationship management (CRM)) መመሪያ የደንበኞችንና የዕጩ ደንበኞችን መረጃዎች አጠቃልሎ ይይዛል፡፡ ይህ ባሕሪው ድርጅቱ ከደንበኛው ወይም ከደንበኛው ወኪል ግለሰብ ጋር የተለዋወጣቸውን መረጃዎች በአጠቃላይ፣ ማለትም ለምሳሌ ቀኑን፣ የስልክ ጥሪ እና ኢሜይል የተደረገባቸውን ጊዜአቶች እንዲሁም ከድርጅቱ ጋር ያደረጉትን የግብይት ታሪካቸውን ያካትታል፡፡ ሲ.አር.ኤም፣ ድርጅቱ ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት እንዲያሻሽል ያደርገዋል፤ ምክንያቱም ሠራተኞች ከደንበኛው ጋር በሚሠሩበት ወቅት የሚስፈልጓቸውን መረጃዎች በአጠቃላይ በቀላሉ እንዲያገኙ ስለሚያስችላቸው ነው፡፡

የሰነድ አስተተዳደር ሥርዓት (Document management systems (DMS))፤ አብዛኛውን ጊዜ ፋይሎችን ወይም ሰነዶችን ለማከማቸት፣ ለማጋራት፣ ለመከታተል እና ለማስተዳደር ጥቅም ላይ የሚውል የኮምፒዩተር ሥርዓት ነው፡፡ አንዳንድ ሥርዓቶች፣ በተለያዩ ተጠቃሚዎች የተፈጠሩና የተስተካከሉ የተለያዩ ሰነዶችን ታሪክ መከታተል የሚያስችል ባሕርይን ጨምረው የያዙ ናቸው፡፡ ቃሉ ከመረጃ አያያዝ አስተዳደር ሥርዓት ጽንሰ አሳቦች ጋር ተወራራሽነት ያለው ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እንደ ድርጅት መረጃ አያያዝ ሥርዓት ተደርጎ የሚታይ ሲሆን፣ ከዲጂታል ንብረት አስተዳደር፣ የወረቀት ሰነዶችን ለኮምፒዩተር ወደሚመች ሰነድነት (document imaging) ከመቀየር ሥራ፣ ከሥራ ፍሰት ሥርዓቶች እና ከመዝገብ አስተዳደር ሥራዎች ጋርም ተያያዥነት ያለው ነው፡፡

የኢ.አር.ፒ ኤሌክትሮኒካዊ የንግድ ልውውጥ ኅብር፣ ውጤታማ የበይነ መረብ ሽያጭ ጣቢያን (channel) ለመፍጠር በሚያስቡ (B2B organizations) ድርጅቶች ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ ታዋቂ/ ተመራጭ ሆኗል፡፡ ለብዙ (B2B) ኩባንያዎች፣ በሥራ ላይ ያለ ኢ. አር. ፒ፣ የተለያዩ ንግድ ሥራ መተግበሪያዎች በአንድነት ተቀናጅተው የሚሠሩበትን መንገድ የሚያረጋግጥ መሣሪያ ነው፡፡ የምርትን ወይም የምርት ዝርዝር መግለጫ ሰነድ አስተዳደርን፣ የኢንፎርሜሽ ቴክኖሎጂ (IT) አገልግሎቶችን፣ የንብረት ቆጠራ ሶፍትዌርን፣ የመጋዘን አስተዳደርን የመሣሠሉ ከጀርባ የሚሠሩ ሥራዎች በተናበበ መንገድ እንዲጠናቀቁ ያግዛል፡፡

የሥራ ብቃት ማስረጃ ሰነድ አስተዳደር፣ የሥራ ብቃት ማሥረጃዎችዎን የማቅረብ፣ የማቀድ፣ እና የመቆጣጠር አቅምዎን የሚደግፉትን የተቀናጀ የሥራ ፍሰትንና የማጽደቅ ሂደቶችን በኅብረት መፍጠር ያስችልዎታል፡፡ በከፍተኛ ደረጃ እንደ ሁኔታው የመቀያየር ባሕሪው፣ በግልጽ ለሚታወቁ የሂደት ቅድመ ሁኔታዎች እንዲመች ተደርጎ መሠራት የሚችል ያደርገዋል፡፡

የሱፐር ቡስት አፕ ኢ.አር.ፒ ፕሮጀክት አስተዳደር፣ የንግድ ሥራዎ ከውስብስብነት እና ከለውጥ ጋር እየታገለ ባለበት ሁኔታ እንኳን፣ እንደየ ሁኔታው ከፍ ያለ የተለዋዋጭነት ባሕርይ እና ምርታማነት increased እንዲኖረው ከፈለጉ፣ እነዚህን ውስብስብ ጉዳዮች ማስተዋልና ማስተዳደር የሚያስችሉዎት እነዚህ መሣሪያዎች ያስፈልጉዎት ይሆናል፡፡ ሥራዎችን በመገምገም፣ በመከለስና በማደስ ወደ ሂደት ደረጃ የሚያወርዱበት መንገድ ይስፈልጎታል፡፡

የትምህርት ቤት አስተዳደር ሥርዓት፣ ዋነኛ ዓላማው የወረቀት ሥራዎችን ወደ ኮምፒዩተር ሥርዓት የማስገባት እና ያለ ብዙ የባለሙያ ጣልቃ ገብነት ሥራዎች የሚሠሩበትን ሁኔታ ማስቻል ቢሆንም፣ ይኸው መድረክ በተማሪዎች፣ በመምህራን እና በወላጆች መካከል መስተጋብር ለመፍጠር ሊያገለግልም ይችላል፡፡ ሥርዓቱን ወደ ኮምፒዩተር አሠራር የመቀየር ሥራ የሚሠራው ተማሪዎችን እና መምህራንን የተመለከቱ ዝርዝር ጉዳዮች በሥርዓቱ ውስጥ ለማከማቸት ሲሆን፣ ይህም ሥርዓቱ የተማከለ እንዲሆን ያደርገዋል፤ የመረጃ መደጋገም ዕድልም ይቀንሳል፡፡

የትምህርት ቤት አስተዳደር ሥርዓት የሚያስገኛቸው ጥቅሞች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

 • ጊዜንና ሃብትን ይቆጥባል፣ 
 • የትምህርት ቤት አስተዳደር ሥርዓትን ያዘምናል፣
 • የሥራ ጫናን ይቀንሳል፣ 
 • የምርታማነት መጨመር፣
 • የተሻሻለ ትብብር እንዲኖር ያደርጋል፡፡

ይህ ሥርዓት 12 ሰፋፊ መመሪያዎች ያሉት ሲሆን፣ እያንዳንዳቸው በርካታ አገልግሎቶች አሏቸው፡፡ 

 1. የተማሪዎች መመሪያዎች፣ 
 2. ትምህርት ነክ መመሪያዎች 
 3. የክፍል መመሪያዎች 
 4. የተማሪዎችን መገኘት መቆጣጠሪያ መመሪያዎች 
 5. የርዕሰ ነገር (Subject) መመርያ 
 6. የፈተና መመሪያዎች፣ 
 7. የፋይናንስ መመሪያዎች፣
 8. የጠቅላላ ተጠቃሚዎች አስተዳደር መመሪያ፣
 9. የቢሮ አስተዳደር መመሪያዎች፣ 
 10. ድረ ገጽ አስተዳደር መመሪያዎች፣ 
 11. የሥርዓት አስተዳደር መመሪያ፣ 
 12. የትምህርት ክፍለ ጊዜ አስተዳደር መመሪያዎች፣

መተግበሪያ ልማት (App Development)

መተግበሪያ ልማት፣ ለስማርት ስልኮች፣ ለታብሌቶች እንዲሁም በአብዛኛው ለአንድሮይድ (Android) እና ለአይ.ኦ.ኤስ (ios) አሠራር ሥርዓቶች ዲጂታል አጋዦች፣ ሶፍትዌር የማዘጋጀት ሂደት ነው፡፡ ይህ ሶፍትዌር በመሣሪያው (ስልክ ወይም ታብሌት) ላይ ቀድሞ ሊጫን፣ ከሞባይል አፕ ስቶር ላይ ሊወርድ፣ ወይም በሞባይል ድረ ገጽ አማካይነት ሊገኝ ይችላል፡፡ ሱፐር ቡስት አፕ፣ ደንበኞችዎ በቀላሉ እንዲያገኙዎትና ተደራሽ እንዲሆኑ የሚያስችሉ መተግበሪያዎች ያጎለብትልዎታል፡፡ በአሁኑ ወቅት፣ በበይነ መረብ አማካይነት የሚካሄድ ግዢ በማኅበረሰባችን እየተለመደና ብዙዎችም ይህንኑ መንገድ የተለመደ የመገበያያ ምርጫቸው እያደረጉት የመጣ ሲሆን፣ የሞባይል መተግበሪያም ይህን ማስፈጸሚያ አንዱ መንገድ ነው፡፡

የሞባይል መተግበሪያ ለምን አስፈለገ?

 • ግብይትን ያመቻቻል፣
 • በደንበኞችዎ በቀላሉ እንዲገኙ ያግዛል፣
 • ጊዜ እና ሃብትን ይቆጥባል፣ 
 • ኩባንያዎን ያዘምናል፡፡
እኛ እምንሰራው

የረቀቁ እና አስተማማኝ
ሶፍትዌር እንገነባዎታለን

amAM