SuperBootsUp

Edit Content

እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ?

ድህረገፅ ዲዛይን

ድህረገጾን አሁን ያግኙ

የፌስቡክ ማስታወቂያዎች

ንግድዎን በፌስቡክ ያሳድጉ

ላንዲንግ ፔጅ

የንግድ ላንዲንግ ፔጅ ያግኙ

SEO

#1 የጉግል ፍለጋ ደረጃ ያግኙ

ጎግል ማስተዋወቂያ

በጎግል ማስታወቂያ ሽያጭዎን ያሳድጉ

የቪዲዮ ፕሮዳክሽን ስራ

ከፍተኛውን የጥራት ደረጃ ተጎናጸፉ የቪዲዮ ማስታወቂያዎች እና ትክክለኛው የማስተዋወቅ ቴክኒክ

ሞዴል እና ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ማስተዋወቅ

ለሞዴሎች እና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ማስተዋወቅ

የኩባንያ ብራንዲንግ፣የአርማ(ሎጎ) ንድፍ (ዲዛይን)

የዲጂታል ግብይት ተሳትፎዎን ከእኛ ጋር ይለኩሱ

የድርጅቶች እና የግለሰቦች ሥልጠና

የድርጅት ሥልጠናና ዕድገት ላይ ኢንቨስት ያድርጉ

ሶፍትዌር ማበልጸግ እና አይቲ መፍትሄዎች

ምርጥ ሶፍትዌር እና የአይቲ መፍትሄዎችን ያግኙ

የስኬታማ ሽያጭ ጥበብ ሚስጥራት መጽሐፍ

ማናቸውንም ነገር ለማንኛውም ሰው መሸጥ የመቻልን ጥበብ ይካኑ!!

የአርማ(ሎጎ) ንድፍ (ዲዛይን)

❝ የዲጂታል ግብይት ተሳትፎዎን ከእኛ ጋር ይለኩሱ ❞

የዲጂታል ግብይት ተሳትፎዎን ከእኛ ጋር ይለኩሱ

የ DigitalBoost አርማ እድገትን፣ ግንኙነትን እና ዲጂታል ለውጥን የሚወክሉ ግብዓቶችን ሊያካትት ይችላል። አቅምን እና ፈጠራን ለማመልከት የደመቁ ቀለሞች ጥምረት ቢጠቀሙ የሚመረጥ ሲሆን፤ ቅጥ ያለው ወደ ላይ ያለ ቀስት ወይንም ደግሞ የመብረቅ ብልጭታ ኩባንያው ለደንበኞቹ የሚያመጣውን እድገት ይወክላል። የፎንት(የፊደላት ቅርፅ) ምርጫዎ ዘመናዊ እና ቀለል ያለ የዲጂታል የግብይት ኢንዱስትሪ ተለዋዋጭ ባህሪን የሚያንፀባርቅ መሆን አለበት።

የሎጎና የ‹ብራንዲንግ› ፍላጎትዎን ለማሟላት፤ ምርጫዎና የቀጥታ መዳረሻዎ ወደ ሆነው ወደ ‹ሱፐርቡት አፕ› እንኳን በደህና መጡ፡፡ ሽሚያና ፉክክር በበዛበት በዛሬው አለም የገባያ አከባቢ ውስጥ፤ ጠንካራና አይረሴ የሆነ ብራንድ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አጥብቀን እንረዳለን፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ የተገኘነውም ለዚህ ነው፡፡ ማለትም፤ ዘላቂ የሆነ ተጽእኖ ማሳደር የሚችልና ልዩ ሆኖ የሚታይ የብራንድ ማንነት ርስዎም እንዲኖረዎት ለማገዝ ብርቱ ፍላጎትና ተነሰሽነት እንዲሁም ብቃት ስላለን ነው፡፡

ሰፊ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎቻችን ውጤት የሚያመጡና የሚያስደምሙ ሎጎዎችን በመፍጠር ረገድ የጋለ ስሜትንና ፈቃደኝነትን የታጠቁ ናቸው፡፡ በደንብ የተነደፈና የተዘጋጀ ሎጎ የእርስዎን የንግድ ስራ ይዘቶችና እሴቶች በቅጡ ሊያንጸባረቅ እንደመቻሉ መጠን፤ የብራንድዎ የፊት ለፊት ገጽታ ማለትም እንደሆነ አጥብቀን እናምናለን፡፡ እንደ ‹ሱፐር ቡስት አፕ› ድርጅተነታችን፤ ባለን የፊደል አወቃቀር ስልትና ገጽታ (typography)፤ እንዲሁም የቀለማት ንድፈ ሃሳብ እውቀትና የግራፊክስ ዲዛይን ክህሎት አማካኝነት፤ ለእርስዎ የሚዘጋጀው ሎጎ የተደራሾችዎን ቀልብ ሰቅዞ የሚይዝ፣ አይረሴና ከፍተኛ ተጽእኖ የሚሳድር እንዲሆን የማድረግ ሙሉ አቅም አለን፡፡

ደግሞም አግልግሎታችን በሎጎ ዝግጅት ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ ከማስታወቂያ ድርጅትነት ባለፈና ከራስዎ የማርኬቲንገ ዲፓርትመንት ጋር በሚስተካከል መልኩ፤አጠቃላይ የሆኑ ሌሎች በርካታ አገልግሎቶችንም እንሰጣለን፡፡ የገባያ ፕላን ከማርቀቅ አንስቶ አሳታፊና ማራኪ የሆነ ‹ይዘት› እስከማዘጋጀት ድረስ ያለውን ሁሉ በአግባቡ በመከወን፤ ብራንድዎ በማናቸውም የገባያ ውድድር ውስጥ ብልጫ እንዲያገኝና እንዲፈረጥም ማድረግ እንችላለን፡፡

‹የሱፐር ቡስት አፕ ባለሙያዎች›፤ የሸማችን እይታ በመሳብና ‹ብራንድ›ን ለይቶ በማሳወቅ ረገድ፤ ቀለማት እጅግ ብርቱ መገልገያ መሆናቸውን አሳምረው ያውቃሉ፤ይረዳሉም፡፡ ስለዚህም፤ ከከለሮቸ ጀርባ ያለውን ስነ-ልቡና ሁሉ፤ ማለትም የሚፈጥሯቸውን ተዛምዶዎችና የሚጫወቱትን ሚና፤ አልፎ ተርፎም በሰዎች ስሜቶች ላይ ሊያሳድሩአቸው የሚችሏቸውን ተጽእኖዎች በሚመለከት ሁሉ ከፍተኛ እውቀትና ግንዛቤ ያዳበሩ ናቸው፡፡ እነሱን ባቀፈው የባለሙዎች ስብስባችን አማካኝነትም፤ የእርስዎን የገባያ ተደራሾች የውስጥ ስሜቶችና ፍላጎቶች የሚቀሰቅሱና አብረው የሚነዝሩ፤ ለዚሀም የብራንድዎን እሴቶች ሁሉ በአመርቂ ሁኔታ ሊያስተላልፉ የሚችሉ ቀለማትንና ውጤታማ ቅንብሮችን ልንፈጥርልዎት እንችላለን፡፡

የአግልግሎቶቻችን አድማስም ቢሆን፤ የብራንዲንግ ፍላጎቶችዎን ሁሉ ለማሟላት በሚያስችል መልክ የተነደፈና የተደራጀ ነው፡፡ ‹ሎጎ› ከመፍጠር አንስቶ እስከ፣ ‹ብራንድ› ማበልጸግና የራስዎ ብቻ የሆነ ‹የብራንድ ማንነት› እስከማዘጋጀት ድረስ ያለውን በሚመለከትም ቢሆን፤ የብራንድዎን ራእይ እውን ለማድረግ የሚያስችል ከፍተኛ የፈጠራ ችሎታና ክህሎት አለን፡፡ እርስዎ ከትንሽ የተነሱ ጀማሪ የንግድ ስራ ሰውም ሆኑ ነባር ካምፓኒ ወደኛ አገልግሎቶቻች ቢቃኙ በእርግጠኝነት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ምክንያቱም ሁሉም አገልግሎቶቻችን የእርስዎን ልዩ ፍላጎቶች በተለይ አድርጎ ለመረዳትና ለማሟላት በሚያስችላቸው መልክ የተደራጁ ናቸው፡፡

‹ሱፐር ቡስት አፕ›ን ሲመርጡ፤ የሚገያኙት ትሩፋት ሁሉ በ‹ሎጎ› ጉዳይ ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሁለንተናዊ በሆነ የብራንድ ስትራቴጂ ዝግጅትና ጉዞ ላይ ለመሳፈርና ለመመንጠቅ እድል እያገኙ ነው፡፡ በኛ በኩል፤ የንግድ ስራዎን ገጽታዎችና የገባያ ተደራሾዎችዎን እንዲሁም የሽያጭ አቅጣጫዎችዎን ሁሉ ጊዜ ወስደን ቅድሚያ ለመረዳት የምንተጋ ከመሆናችንም በላይ፤ ጥልቅ የሆነ ሙያዊ ምርምርና ትንተና (ጥናት) በማካሄድ፤ ጠንካራና አዛማጅ የብራንድ ማንነት ለመፍጠር የሚያስችል ስትራቴጂን የመዘርጋት አቅምም ያለን ነን፡፡

ግባችንም፤ ከፍተኛ የማስታወቂያ ወጭዎችን በመቀነስና የድርጅትዎን የአትራፊነት ደረጃ በማሸሻል የላቀ ውጤት ማምጣት ነው ፡፡
የ‹ሱፐር ቡስት አፕ› ባለሙያዎች እንደመሆናችን መጠን፤ ለግል ተሞከሮና ልምድም ሆነ ለጋራ ትብብር ከፍተኛ ዋጋ እንሰጣለን፡፡ እያንዳንዱ ንግድ ስራ የየራሱ የሆነ የግል ገጽታ እንዳለው ስለምንረዳ፤ የእርስዎም የብራንድ ራእይ እውን እንዲሆን ከእርስዎ ጋር በቅርበት ተባብረን እንሰራለን፡፡ ከምንናገረው ሁሉ ባሻገር ደግሞ ‹ፖርትፎሊያችን› በራሱ ሰለኛ ብዙ ነገር ይነግርዎታል፡፡ ምክንያቱም ለበርካታና አይነተ ብዙ ለሆኑ የንግድ ስራዎችና ድርጅቶች፤ ውጤታማ የ‹ብራንድ ማንነት› በመፍጠር ረገድ ያለንን ሙያዊ ክህሎት ሁሉ በዝርዝር የሚያሳዎት ‹ፖርተፎሊዮ› ነው፡፡ ብራንድዎን ወደ ሚቀጥለው ከፍተኛ ደረጃ ማሸጋገር ይሻሉ? ፍላጎቶችውን ሁሉ ለመረዳት እንድንችል አሁኑኑ ያግኙንና እንነጋገር፡፡ የብራንድዎን ጎልቶ የመታየትና የመታወቅ ደረጃ እንዲሁም ስኬት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርም አብረን እንጓዝ፡፡ ‹ሱፐር ቡስት አፕ›፤ ከርስዎ ጋር ተባብሮ ለመስራትና በዚህም፤ ብራንድዎ ከማናቸውም ጊዜ በላይ ፈክቶና ደምቆ እንዲታይ ለ ማድረግ ብርቱ ፍላጎትና ጉጉት ያለው ድርጅት ነው፡፡
እኛ እምንሰራው

ሰዎች የኦንላይን ቢዝነስ
እንዲደራጁ መርዳት ነው

amAM