SuperBootsUp

Edit Content

እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ?

ድህረገፅ ዲዛይን

ድህረገጾን አሁን ያግኙ

የፌስቡክ ማስታወቂያዎች

ንግድዎን በፌስቡክ ያሳድጉ

ላንዲንግ ፔጅ

የንግድ ላንዲንግ ፔጅ ያግኙ

SEO

#1 የጉግል ፍለጋ ደረጃ ያግኙ

ጎግል ማስተዋወቂያ

በጎግል ማስታወቂያ ሽያጭዎን ያሳድጉ

የቪዲዮ ፕሮዳክሽን ስራ

ከፍተኛውን የጥራት ደረጃ ተጎናጸፉ የቪዲዮ ማስታወቂያዎች እና ትክክለኛው የማስተዋወቅ ቴክኒክ

ሞዴል እና ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ማስተዋወቅ

ለሞዴሎች እና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ማስተዋወቅ

የኩባንያ ብራንዲንግ፣የአርማ(ሎጎ) ንድፍ (ዲዛይን)

የዲጂታል ግብይት ተሳትፎዎን ከእኛ ጋር ይለኩሱ

የድርጅቶች እና የግለሰቦች ሥልጠና

የድርጅት ሥልጠናና ዕድገት ላይ ኢንቨስት ያድርጉ

ሶፍትዌር ማበልጸግ እና አይቲ መፍትሄዎች

ምርጥ ሶፍትዌር እና የአይቲ መፍትሄዎችን ያግኙ

የስኬታማ ሽያጭ ጥበብ ሚስጥራት መጽሐፍ

ማናቸውንም ነገር ለማንኛውም ሰው መሸጥ የመቻልን ጥበብ ይካኑ!!

የቪዲዮ ፕሮዳክሽን፤ ለብራንድዎ ተጨባጭ ውጤት ለማግኘት ማስታወቂያዎ ፈጠራ እና በየጊዜው እየረቀቀ ከሚመጣው ቴክኖሎጄ ጋር የሚጓዝ አገልግሎ በእርግጥ ያስፈልጎታል

በላቀ ደረጃ ቪዲዮ ቅንብርን፤ ከስትራቴጂያዊ የማስታወቂያ ቅንብሮች ጋር አዋህዶ በማቅረብ ወደ ሚታወቀውና የማርኬቲን ድርጅት ቁንጮ ወደሆነው ወደ ‹ሱፐር ቡሰት አፕ› እንኳን በደህና መጡ፡፡ የቅርብ ጊዜ ቴክኖሎጂዎችንና ከፍተኛ ክህሎት ያላቸውን  ባለሙያዎችን በማጣመር ልዩ የቪዲዮ ቅንብሮችን ማቅረብ የምንችል በመሆናችን ኩራት ይሰማናል፡፡ ከዚህ አገልግሎታችን በተጨማሪ፤ እንደ ፌስ ቡክ(Facebook)፣ ኢንስታገራም(instagram)፤ ዩቲዩብ(youtube)፣ ቲከቶከና(Tiktok) የመሳሰሉ መድረኮችን የመጠቀም ደረጃና ልምድን በማሳደግና ምርቶችዎን ለገባያ ተደራሾችዎ በአግባቡና በከፍተኛ ብቃት በማስተዋወቅ ረገድ ከማንም በተለየ ሁኔታ እጅግ የተካንን መሆናችንን በደስታ እንገልጽልዎታለን፡፡

ፈጠራ በተሞላበት የተዘጋጁ ቀልብ ሳቢ የሆኑ የማስታወቂያ ፎርማቶች (ስራዎች)

‹ሱፐር ቡስት አፕ› ተደራሾችን በመሳብና ተሳታፊ በማድረግ፤ በዚህም ውጤት በማምጣት  ረገድ፤ ፈጠራ ያለውን ሃይልና አመርቂነት ይገነዘባል፡፡ በጥብቅ ያምንበታልም፡፡ ፈጠራዊ ሥራዎቹ በተለየ ሁኔታ ለደንበኞቻችን ምርቶች ተስማሚ እንዲሆኑ ተደርገው በልዩ ሁኔታ የሚዘጋጁ እና ጠንካራ የግንኙነት ሥልቶች ላይ የሚገነቡ ናቸው፡፡ ሊፈጽሙት ያቀዱት ጊዜን ከግምት ያስገባ ዕቅድ ካለዎት፣ በሱፐር ቡስት አፕ ውስጥ የሚገኙ የብቃት ጥግ ላይ የደረሱት ባለሙያዎቻችንና ስብስባቸው፤ ተቀናጅተው ሕልምዎን ዕውን በማድረግ ማናቸውንም ሁካታና ጫጫታ ዘልቆ በመውጣት ጎልቶ የሚታይ፤ በዚህም ዘላቂ ተጽእኖ የሚያሳድር የማስታወቂያ ፎርማት በማዘጋጀት ረገድ እጅግ የተካንን ነን፡፡ እንደ ሱፐር ቡስት አፕ፣ ዋነኛው ዓላማችን ከሌላው ጋር ተመሳስለንና ተደብቀን የመኖር ጉዳይ አይደለም፡፡ በገበያው ውስጥ መገኘትዎ እንዲታወቅ ከፈለጉ፣ ሱፐር ቡስት አፕ፣ መገኘትዎ እንዲታይ፣ እንዲሰማና እንዲታወቅ ያደርግልዎታል፡፡ ሱፐር ቡስት አፕ እያንዳንዱ የማስታወቂያ አቀራረብ የደንበኞቹን ዋነኛ ግቡን መምታቱን ለማረጋገጥ ይችል ዘንድ፣ ዓይነ ግቡ የማስታወቂያ ጽንሰ አሳቦችን፣ አቀራረቦችን፣ እንዲሁም ዝርዝር ሥራዎችንና ይዘቶችን በመቅረጽ ውጤታማ በሆነ መንገድ ይቆጣጠራል፡፡በተደጋጋሚ ያስመዘገብናቸው ውጤቶች፣ የፈጠራ ሥራዎቻችን በገበያው ውስጥ ከሁሉ የላቁ ናቸው፡፡ ይህን እንደ ማዕዘን ድንጋይ የጠነከረ (አንቱታን ያስገኘልንን) ሥራችንን የምንኮራበት ሲሆን፣ የዚሁ ድንቅ ሥራችን ማሳያ የሆኑ ሥራዎቻችንን ዝርዝር እንደሚከተለው ስናቀርብ በደስታ ነው፡፡

ሥራችን የሚከተሉትን ዘርፎች ያካትታል

  • የቪድዮ ማስታወቂያ ሥራዎችን ወይም ቪዲዬ ፕሮዳክሽንና ፎቶግራፍ ማንሣት:
  • ሞዴልስ እና ኢንፍሎሰር በመጠቀም ማስተዋወቅ
  • የዲጂታል ሚዲያዎች እና መገናኛ ብዙሃን ላይ ማስተዋወቅ Media Planning and Placement
    1. ሶሻል ሚዲያ (social media) ማስታወቂያ
    2. ቴሌቪዥንንና ሬዲዮንን፤ የሚያካትት ማስታቂያዎች
  • የንግድ መለያ ምልክትና ሥያሜ ዝግጅት፣ (logo design and branding)
  • ማስታወቂያዎችን ዲዛይን ማድረግ (graphics design)
  • የኹነቶችንና የማስታወቂያ ሥራዎችን ንድፍ የማዘጋጀት ሥራ event and promotion design….

ቪዲዬ ፕሮዳክሽንና ፎቶግራፍ ማንሣት

ደንበኛ ተኮር እና ከፍተኛ ጥራት ያለው የቪዲዮ ቅንብር ደረጃና የስራ ሂደት ሱፐር ቡስት አፕ አጠቃላይ የሆነ የፕሮዳክሽን አገልግሎት የምንሰጥ ሲሆን ይህም Videography(ተንቃሳቃሽ ምስል)ን እና Photography(ምስል) ያጠቃልላል። እኛ የምንከተለው የ process oriented development ፕሮዳክሽን ለማዘጋጀት የሚፈጀውን ጊዜ፣ ወጪ እና ሪስክ ሚቀንስ ይሆናል። በፕሮፊሽናል ባለሙያ የሚሰራ የፕሮዳክሽን ስራ ድርጅትዎ ትልቅ ትርፍ፣ ብዙ ተመልካችን የሚስብ እና ትክክለኛውን ደንበኛ እና የስራ አጋር እንዲያገኙ ያደርጋል።
አብዛኞቹ የቪዲዮ ፕሮዳክሽንና የፎቶግራፍ ሥራዎች፣ ለተለያዩ የዲጂታል እና ለቴሌቪዥን ለማስታወቂያ የሚጠቅሙ ሲሆን፣ በተለያየ ቦታ እና በስቱዲዮ ውስጥ የሚሰሩ ናቸው፡፡

እኛ የ‹ሱፐር ቡስት አፕ› ባልደረቦች፤ ማናቸውም፣ ብራንድ የራሱ የሆኑ ልዩ ገጽታዎችና መስፈርቶች እንዳሉት እንረዳለን፡፡ ለዚህ ነው፤ የእርስዎን ልዩ ፍላጎት መሰረት ያደረጉና ‹ደንበኛ ተኮር› የሆኑ የቪዲዮ አቅርቦቶችን የምንሰራልዎ፡፡ አሁን ላይ ርስዎ የሚሹት፤ የ‹ብራንድ ማሳወቂያም ሆነ አዲስ ምርት የማስተዋወቅ ተግባር፤ አሊያም ደግሞ ቀልብ ሳቢ ሆነ ዶክመንተሪ ማቀናበርና ማቅረብ፤ የኛ የሙያተኞች ስብስብ ደግሞ፤ ከራስዎ ራእይ ጋርም ሆነ ኢላማ ካደረጓቸው ተደራሾች ፍላጎት ጋር የሚጣጣምና

ተገቢ የሆነ የቪዲዮ ጽንሰ ሃሳብ ለማበልጸግ ከእርስዎም ጋር ተባብሮ ይሰራል፡፡ አስደማሚ የጥራት ምስል ባላቸው ቪዲዎች አማካይነት ሃሳቦችዎ ሁሉ ነፍስ እንዲዘሩ ማድረግ የምንችል በመሆናችን እንኮራለን፡፡

ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸው መገልገያዎች

ሱፐር ቡስት አፕ፤ የቪዲዮ ቅንብር ስራንና አቅርቦትን በተመለከተ፤ በየጊዜው እየረቀቀ ከሚመጣው ቴክኖሎጄ ጋር በፊትአውራሪነት እየተሰለፈ ስራውን የሚያዘምንና የሚያቀላጥፍ ድርጅት ነው፡፡ ከፍተኛ የሆነውን የምርት ወይንም የአቅርቦት እሴትና ውጤት ለማረጋገጥ፤ ጥበባዊ መገልገያዎችንና ፕሮፌሽናል(professional) ካሜራዎች፣ የቅርብ ቴክኖሎጂዎችን ሁሉ እንጠቀማለን፡፡ ስለዚህም ሙያተኞቹ ሆኑ የምናቀርብሎት በጣም ዘመናዊ በሆኑ የቪዲዮ መገልገያ ቴክኖሎጂዎች የታጠቅን በመሆናቸው የቪዲዮ ማስታወቂያዎች ሁሉ ከፍተኛውን የጥራት ደረጃ ተጎናጸፉ ናቸው፡፡  የምስል ጥራት ደረጃቸው ከፍተኛ ከሆኑ ካሜራዎች ጀምሮ እሰከ ተራቀቁ light system የመብራት፣ የድምጽ እና ቪዲዮ ማቀናበሪያ (ኤዲትኒንግ) ሶፍትዌሮችም ድረስ ያሉትን ሁሉ በከፍተኛ ክህሎት በመጠቀም ራእይዎን እውን ለማድረግ የሚያስችለን አቅርቦትና አቅም አለን፡፡ ከኢንዱስትሪዎች እድገቶችና ተለዋዋጭ አቅጣጫዎች ጋር ራሳችንን እያደስንና እያሳደግን ለመጓዝ ባለን ጽናት ምክንያት፤ ከሁሉም የላቁና ልዩ የሆኑ ቪዲዎችን በማቀነባር በተደራሾቻችን ሁሉ ላይ ዘላቂ የሆነ ተጽእኖ ማሳደር የቻልን ነን፡፡

ልዩ የሙያ ክህሎት ያላቸው ባልደረቦች ስብስብና የትብብር ሂደት

ተሰጥኦ ባላቸው ባለሙዎች የተደራጀው የቪዲዮ ፕሮዳክሽን ስራ ቡድናችን የካበተ ልምድና ከፍተኛ ክህሎት ያላቸውን ዳይሬክተሮች፣ የፈጠራ ችሎታቸው እጅግ የዳበረ የሲኒማቶግራፊ ባለሙያዎች፣ ኤዲተሮችና ግራፊክስ ዲዛይነሮችን ያካተተ ከመሆኑም በላይ፤ ባልደረቦቻችን ሁሉ እጅግ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ቪዲዮች ለማቅረብ ሲሉ ሁሌም በጥምረት የሚሰሩ ናቸው፡፡ የኛ ባለሙያዎች ስብስብ እንደ የሙያ ዘርፎቻቸው እጅግ የተካኑ ፕሮፌሽናሎች ናቸው፡፡ የሚፈልጉት ቪዲዮ በሚሰራልዎት ጊዜና በሂደቱ ውስጥ፣ ማለትም የቅድመ ቅንብርን(story board) እቅደ ከማውጣት ጀምሮ እስከ መጨረሻው የኤዲቲንግ ስራ ድረስ፤ ከእርስዎ ጋር በቅርበት በመስራት የምቀናበርልዎ ቪዲዮ፤ ከ‹ብራንድዎ› የመለያ ማንነት ጋር መጣጣሙንና አስፈላጊውን መልእክት በቅጡ ማስተላለፉን፤ በዚህም አማካይነት ውጤት ማምጣት መቻሉን ለማረጋገጥ እስከመጨረሻው ተግተን እንሰራለን፡፡ ለሁሉም ክፍት በሆነ ግልጽ የትብብር መንፈስ የምናምን በመሆናችን ደንበኞቻችንም ቢሆኑ የሂደቱ ሁሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ እናደርጋለን፤ ምክንያቱም ደንበኞቻችን የሚሰጡን አስተያየት ሁሉ ለኛ ትልቅ ግብአት ከመሆኑም በላይ፤ የመጨረሻው አላማችንና ግባችን፤ የእርስዎ የደንበኛቻችን እርካታ ብቻ ነው፡፡

ፎቶግራፊ እና አርት ዳይሬክት

ሁለንተናዊ የሆኑ የማስታወቂያ ስራዎች፤ ተገቢና ተመጣጣኝ የሆነ ማኔጅመንትና፤ Digital ገጽታዎችን ሁሌም ወደላይ የማሳደግ ብርቱ ጥረት እንደሚያስፈልጋቸው ቀድመን የተረዳን ነን፡፡ ስለዚህ ማናቸውንም የማስታወቂያዎችዎን ገጽታዎች ሁሉ፤ ከመጀመሪያው የእቅድና የስትራቴጂ ንድፍ ጀምሮ እስከ ተግባራዊነቱነ ፍጻሜ ድረስ እያንዳንዱን ጥቃቅን እንቅስቃሴ እንከታተላለን፤ እንቆጣጠራለን፡፡ ያለማቋረጥ ቁልፍ የሆኑ ሂደቶችንና አፈጻጸሞችን በመተንተን፤

ኢንፎርሜሽን ላይ የተመሰረቱ ማሻሻያዎችን እናድረጋለን፡፡ በዚህም የእርስዎ ማስታወቂያዎች የመጨረሻውን ተፈላጊ ውጤት ማምጣት መቻላቸውንና አለመቻላቸውን እንቆጣጠራለን፡፡

አጠቃላይ የማስታወቂያ ማኔጅመንት እና ሪፖርት ውጤቶችን ወደ ከፍታ ለማውጣት

በ‹ሱፐር ቡስት አፕ› ውስጥ፤ ዋናው ትኩረታችን፤ ልዩ የሆነ የቪዲዮ ቅንብርና ለብራንድዎ ተጨባጭ ውጤት የሚያስገኙ የማስታወቂያ አገልግሎቶችን ማቅረብ ነው፡፡ ባለን የፈጠራ እምቅ ሃይልና ችሎታ፤ እንዲሁም የእርስዎን የፕሮፌሽናል ደረጃ ለማሳደግና፤ በዚህም እርስዎን ስኬታማ ለማድረግ የምናደርገው ጥረት አመርቂ ውጤት እንሚያስገኝሎት እርግጠኛ ነን፡፡

ሁለንተናዊ የሆኑ የማስታወቂያ ስራዎች፤ ተገቢና ተመጣጣኝ የሆነ ማኔጅመንትና፤ ገጽታዎችን ሁሌም ወደላይ የማሳደግ ብርቱ ጥረት እንደሚያስፈልጋቸው ቀድመን የተረዳን ነን፡፡ ስለዚህ ማናቸውንም የማስታወቂያዎችዎን ገጽታዎች ሁሉ፤ ከመጀመሪያው የእቅድና የስትራቴጂ ንድፍ ጀምሮ እስከ ተግባራዊነቱነ ፍጻሜ ድረስ እያንዳንዱን ጥቃቅን እንቅስቃሴ እንከታተላለን፤ እንቆጣጠራለን፡፡

ያለማቋረጥ ቁልፍ የሆኑ ሂደቶችንና አፈጻጸሞችን በመተንተን፤ ኢንፎርሜሽን ላይ የተመሰረቱ ማሻሻያዎችን እናድረጋለን፡፡ በዚህም የእርስዎ ማስታወቂያዎች የመጨረሻውን ተፈላጊ ውጤት ማምጣት መቻላቸውንና አለመቻላቸውን እንቆጣጠራለን፡፡

የማስታወቂያ ዘመቻዎችዎን አፈጸጻምና ውጤትም ከስር ስር እንከታተላለን፡፡ እንደ ‹conversion፣ ‹click through rate› እና ‹impressions› ያሉ ሜትሪክሶችን በመተንተን፤ ስለተደራሾችዎ ባህርይም ሆነ ስለማስታወቂያ ዘመቻው ውጤታማነት ዋጋ ያላቸው ግንዛቤዎችን እናዳብራለን፡፡

ይህ ኢንፎርሜሽን ተኮር የሆነ አቀራረብ፤ በመረጃና በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ውሳኔዎችን እንድንወስንና፤ ከፍተኛ ውጤት የሚያስገኙ ቀጣይ ዘመቻዎችን እንድንቀይስ ያስችለናል፡፡‐‑የማስታወቂያ ዘመቻዎችዎ ሳያቋርጡ እየተሻሻሉ እንዲሄዱና ሁሌም አመርቂ ውጤት የሚያስገኙ እንዲሆኑ ለማድረግ በጽናት የቆምን ነን፡፡

በማያቋርጥ ክትትልና ትንተና አማካይነት፤ መሻሻል የታየበቻውን ገጽታዎች እየለየንና ሁሌም የበለጠ እንዲሆኑ በማስቻል፤ ከንግድ ስራዎ ከፍተኛ የሆነ ተመላሽ ገቢ እንዲያገኙ በከፍተኛ ደረጃ እንሰራለን፡፡

የምንቀርባቸው ሪፖርቶችም፤ የስኬትዎን ደረጃ ለመለካትና ወደፊት የሚያኪያሄዷቸውን የማስታወቂ ዘመቻዎች በተመለከተ በእውቀት ላይ ተመሰረተ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡

የዲጂታል ሚዲያዎች እና መገናኛ ብዙሃን ላይ ማስተዋወቅ

እንደ ፌስ ቡክ፣ ኢንስታገራም፣ ዩ ቲዩብና ቲክቶክ ካሉ መድረኮች በተጨማሪ፤ ሌሎች አይነቶችንም በማካተት መድረከ- ብዙ የሆነ ማስታወቂያ የማካሄድ አስፈላጊነትን እንረዳለን፡፡ስለዚህ፤ የማስታወቂያወቻችንን ተደራሽነት ለማስፋትና አንደምታቸውን ለማሳደግ፤ ሌሎች መድረኮችንና ማስተላለፊዎችንም ዘወትር እያሰስን እንጠቀማለን፡፡ 

ይህም፤ ነባር የሆኑ እንደ ቴሌቪዥንንና ሬዲዮንን፤ የሚያካትት ነው፡፡ ስትራቴጂያዊ በሆነ መንገድ ተገቢዎቹን ሚዲያዎች በመምረጥና በማጣመር፤ የእርስዎ የማስታወቂያ መልክቶች ኢላማ ወደአደረጓቸው ተደራሾች  መድረሳቸውንና ብራንድዎም ልዩና ጎልቶ የሚታወቅ መሆኑን በሚያረጋግጥ መንገድ ስራችንን እንሰራለን፡፡

ሶሻል ሚዲያ ማስታወቂያ

በዛሬው ዲጂታላዊ(digital) አለም ውስጥ፤ ሶሻል ሚዲያ (social media) መድረኮች ማስታወቂ በማሰራጨትና ለብዙ የገባያ ኢላማዎች ተደራሽ በመሆን ረገድ ብርቱና ፍቱን መገልገያዎች ሆነዋል፡፡

የፌስቡክና የኢንስታገራም ማስታወቂያዎች—እነዚህ ሁለቱ በቢሊዮኖች ሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ስላሏቸው፤ የገባያ ተደራሾችን በስፋት ለማገግኘት ሰፊ እድል የሚሰጡ ናቸው፡፡የኛ የባለሙያዎች ስብስብ፤ የቪዲዮና የፎቶ ማስታወቂያ የመሳሰሉትን ቴክኒኮች ከማራኪ ትረካ ስልት ጋር በመጠቀም ከተደራሸችዎ ፍለጎትና ልብ ጋር አብሮ የሚነዝርና ቀልብ ሳቢ የሆነ የማስታወቂያ ዘመቻ እንሰራልን፡፡

የቲክቶክ ማስታወቂያ—ወጣት የሆኑ ተደራሾችን ስርጭትን በሚመለከት ቲክ ቶክ ሁነኛና ዝነኛ መድረክ ለመሆን በቅቷል፡፡ እኛም የዚህን መድረክ ተጠቃሚዎች ቀልብ የሚስብ ዝነኛ የማስታወቂያ ዘመቻ ማካሄድ እንዲቻል፤ የዚህን መድረክ አቅርቦቶች አንጠፍጥፎ ለመጠቀም የሚስችሉንን ስልቶች ሁሉ በጥንቃቄ ነድፈናል፡፡

የዩቲዩብ ማስታወቂ-ያ—ዩ ቲዩብ ለቪዲዮ ቅንብርና ማስታወቂያ አይነተኛው መድረክ ሲሆን፤የኛ ባለሙያዎች ቡድን፤ ከመድረኩ ገጽታዎችና ባህርያት ጋር አብረው የሚሄዱና ተለያዩ የሆኑ የማስታወቂያ ስልቶችን ይነድፋል፡፡ የ‹ፕሪ ሮል›(pre roll) ማስታዎቂያዎችንም ሆነ ማስታወቂዎችን እንዲሁም የገጽ አናት ላይ ‹ደባል ቪዲዎችን›፤ ወዘተ በሚመለከት የምናቀነባብራቸውን የዬ ቲዩብ ማስታወቂዎቻችንን፤ ከተመልካቾች ፍለጎት ጋር አብረው የሚሔዱና ተግባራዊ ደንበኞችን በፍጥነት ለማፍራት የሚያስችሉ እንዲሆኑ ማድረግ ችለናል፡፡

ከነዚህ መድረኮች በተጨማሪ፤ ብራንድዎን ለማስተዋወቅ የሚያስችሉ ሌሎች ተጓዳኝ መድረኮችንም እያሰስን በጥቅም ላይ እናውላለን፡፡ ይህን የምንከውነውም የነደፍነውን ስትራቴጂ ሁሉ ከአዲስ አይነቶቹ መድረኮች ጋር እንዲጣጣሙ ለማድረግ እንደ ተጠቃሚዎች ዴሞግራፊ፣ የባህርይና የምርጫ አዝማሚያና፤ እንዲሁም ማስታወቂያ የመልቀቅ አማራጮችን በማጤንና ስልት በመቀየስ ነው፡፡ ምክንያቱም የመጨረሻው አላማችን የእርስዎ ብራንድ በተገቢው ደረጃ መተዋወቁንና ውጤት ማምጣቱን ማረጋገጥ ነው፡፡

ቴሌቪዥንንና ሬዲዮንን፤ የሚያካትት ማስታቂያዎች

ሱፐር ቡስት አፕ፣ ደንበኞቹን ወክሎ በተአማኒ የሚዲያ አውታሮች ላይ ማስታወቂያ ማስነገር የሚያስችለው ሙሉ ዕውቅና አለው፡፡ ከሁሉም ሚዲያዎች ጋር በጣም ጥሩ ግንኙነት ያለው በመሆኑም፣ ጥሩ ዋጋዎችንና የመሥሪያ ቦታዎችን ለማግኘት የሚያስችሉ ድርድሮችን የማድረግ፣ እንዲሁም ሚዲያዎች ውስጥ ልዩ ዕድሎች ሲኖሩ መረጃውን ቀድሞ የማግኘት አቅም አለው፡፡

የሱፐር ቡስት አፕ ባለሙያዎች ቡድን የደንበኛን የሸመታ ዓውድ በሚመለከት የጠለቀ እውቀት ያለው ነው፡፡ የሕዝብን ስብጥር፣ እንዲሁም የደንበኞችን የማየት፣ የማንበብ እና የማዳመጥ ልማዶችን ከግምት ያስገባ ትንታኔና ግምገማ ካደረገ በኋላ፣ የተሻለውን የሚዲያ አማራጭ ይጠቁማል፡፡

የሚዲያ መርሐ ግብር ዕቅድ ዝግጅታችን፣ በተአማኒ ሚዲያዎች ላይ መረጃው እንዲደርሳቸው ለሚፈለጉ አካላት የሚነገርበት ተገቢና ትክክለኛ ሁኔታ ላይ በመመሥረት የሚካሄድ ነው፡፡

ሞዴሎች እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን መጠቀም ስትራቴጂ

 

ድርጅቶች ሞዴሎችን ወይም ተፅዕኖፈጣሪዎችን በመጠቀም በዲጂታል/ሶሻል ሚዲያ ማስተዋወቅ፡፡ ሶሻል ሚዲያዎች ልክ እንደ ኢንስታግራም፤ ቲክቶክ፤ ዩቱዩብ አንዲሁም ቴሌቪዥንንና ሬዲዮንን፤ ሞዴሎችን እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን በመጠቀም
ለማስተዋወቅ አሪፍ አማራጮች ናቸው፡፡ በጣም ማራኪ፣ ለዕይታ ሚስቡ እና አይረሴ ምስሎችን እና ቪድዮችን በመስራት ለተፈለገው ተመልካች ማድረስ ይቻላል፡፡

የምርት ክፍል ቡድናችን ከተለመደው ወጣ ያሉ የምርት መለያዎችንና ምልክቶችን በመፍጠር ረገድ ዝናን ያተረፈ ነን፡፡

www.superboostup/models and influencers.com

ብራንዲንግ እና ሎጎ ዲዛይን

የንግድ ምልክትን የማሳወቅ ሥራ፣ መረጃው እንዲደርሳቸው በሚታሰቡ ሰዎችና በሸማቾች አእምሮ ውስጥ፣ የንግድ ሥራውን (ምርቱን ወይም አገልግሎቱን) የተመለከተ ልዩ ትውስታ የመቅረጽ ሂደት ነው፡፡ Brand በመሠረታዊ ደረጃ፣ የንግድ ምልክት (ሎጎ)፣ የድርጅቱን መለያ መልእክት(ብራንድ) አጠቃላይ የድርጅቱ ንድፍ፣ ተልእኮን እና ድምፀትን አጠቃልሎ በአንድነት የያዘ ነው፡፡ ዋነኛው መታወቂያ ሥራችን የንግድ ወይም የምርት ብራንድ መገንባት ነው፡፡ የማስታወቂያ ድርጅት ብቻ አይደለንም፡፡ ሁሉ ነገሩ የተሟላለት አንድ የገበያ ጥናት የሥራ ክፍል የሚሰጣቸውን ሙሉ አገልግሎቶች እንሰጣለን፡፡ ከፍተኛ ውጤቶችን የሚያስመዘግቡ የገበያ (የንግድ ሥልቶችን በመቅረጽ፣ በአነስተኛ የማስታወቂያ ወጪ የሚፈለገውን ዓላማ ከማሳካት አንጻር አዎንታዊ ውጤቶች እንዲያገኙ በማድረግ ደንበኞቻችንን ወደትርፍ ጎዳና እንዲጓዙ እናደርጋለን፡፡

እስከማዘጋጀት ድረስ ያለውን በሚመለከትም ቢሆን፤ የብራንድዎን ራእይ እውን ለማድረግ የሚያስችል ከፍተኛ የፈጠራ ችሎታና ክህሎት አለን፡፡

እርስዎ ከትንሽ የተነሱ ጀማሪ የንግድ ስራ ሰውም ሆኑ ነባር ካምፓኒ ወደኛ አገልግሎቶቻች ቢቃኙ በእርግጠኝነት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ምክንያቱም ሁሉም አገልግሎቶቻችን የእርስዎን ልዩ ፍላጎቶች በተለይ አድርጎ ለመረዳትና ለማሟላት በሚያስችላቸው መልክ የዘጋጁ ናቸው፡፡

ዋነኛው መታወቂያ ሥራችን የንግድ ወይም የምርት ብራንድ መገንባት ነው፡፡ የማስታወቂያ ድርጅት ብቻ አይደለንም፡፡

ሁሉ ነገሩ የተሟላለት አንድ የገበያ ጥናት የሥራ ክፍል የሚሰጣቸውን ሙሉ አገልግሎቶች እንሰጣለን፡፡  ከፍተኛ ውጤቶችን የሚያስመዘግቡ የገበያ (የንግድ ሥልቶችን በመቅረጽ፣. በአነስተኛ የማስታወቂያ ወጪ የሚፈለገውን ዓላማ ከማሳካት አንጻር አዎንታዊ ውጤቶች እንዲያገኙ በማድረግ ደንበኞቻችንን ወደትርፍ ጎዳና እንዲጓዙ እናደርጋለን፡፡

Super Boots up Branding & Logo Design Service

ማስታወቂያዎችን ዲዛይን ማድረግ

ከፍተኛ ውጤቶችን የሚያስመዘግቡ የገበያ (የንግድ) ሥልቶችን በመቅረጽ፣አነስተኛ የሚባል የማስታወቂያ ወጪ ብቻ እንዲያወጡ በማድረግ እንዲሁም የሚፈለገውን ዓላማከማሳካት አንጻር አዎንታዊ ውጤቶች እንዲያገኙ በማድረግ ደንበኞቻችንን እናግዛለን፡፡

የኹነቶችንና (ኢግዚብሽን /ባዛር) የማስታወቂያ ሥራዎችን ንድፍ የማዘጋጀት ሥራ

በ Super boost up የተካነውን የማስታወቂያ ንድፋችንን በመጠቀም ብቻ ሊረሱት የማይችሉትን ዝግዘጅት እና የተለያዩ ማስተወቂያዎችን ማዘጋጀት ይችላሉ። በዘርፉ የተካኑት ባለሞያዎቻችን በአንድ እይታ ብቻ ትልቅ ተጽእኖ መፍጠር የሚችሉ አስደናቂ መልዕክቶችን ያዘጋጁሎታል፤ ሰራተኞቻችንም ለእያንዳንዱ ትናንሽ ነገር ትኩረት ስለሚሰጡ እና በትጋት ስለሚሰሩ ለተደራሽ ምቹ በሆነ መንገድ መልዕክትዎ ይደርሳል። የእኛን አገልግሎት በመጠቀም ተከታይዎትን ያሳድጉ፣ የንግድዎን መልእክት ተደራሽነትም ያስፉ። ማራኪ ውጥኖችን ለዓይን በሚማርኩ የማስተዋወቂያ ቁሳቁሶች ተጠቅመን በዲጂታል ግብይት እንቅስቃሴዎ አዲስ ከፍታ ላይ እናደርስዎታለን። እርሶ ብቻ ጉዳዩን በእኛ ይጣሉት!

የእኛ ሥራ

የማስታወቂያ አገልግሎቶች፣ የሚዲያ ዕቅድና የውክል ማስታወቂያ ሥራዎች፣ የቴሌቪዥንና የሚዲያ ፕሮዳክሽን፣ የሕዝብ ግንኙነት፣ ኹነቶችን (ዝግጅቶችን) ማካሄድ፣ የጠቋሚ (መረጃ ሰጪ) ማስታወቂያ ምልክቶች፣ግራፊክ ዲዛይን፣ ፎቶግራፍ ማንሣት እና የኪነጥበብ (አርት) ዳይሬክቲንግ ሥራዎች፡፡

ተልዕኮአችን

የድርጅታችን ተልዕኮ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዕድሎችን ወይም አቅሞችን በመጠቀም፣ ጥራት ያላቸው የግብይት መፍትሔዎችን በማቅረብ ረገድ ከፍተኛ ብቃትን መጎናጸፍ፡፡

ተልዕኮአችን –የድርጅታችን ተልዕኮ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዕድሎችን ወይም አቅሞችን በመጠቀም፣ ጥራት ያላቸው የግብይት መፍትሔዎችን በማቅረብ ረገድ ከፍተኛ ብቃትን መጎናጸፍ፡፡ 

ተጨማሪ አገልግሎቶች –የፈጠራ አሳቦችና የኪነጥበብ (አርት) ሥራዎች፣ የንግድ ሥያሜ ሥልቶችና አገልግሎቶች፣ የግብይትና የማማከር አገልግሎቶች፣ የምርት ማስተዋወቅ ሥራዎችን ማቀድና መተግበር፣

amAM