SuperBootsUp

Edit Content

ድህረ-ገፅ ማበልፀግ

ንግዶን የሚያሳድግ ውጤታማ እና አስተማማኝ ድህረ ገፅ ከኛ ያገኛሉ

የቪዲዮ ፕሮዳክሽን

ከፍተኛውን የጥራት ደረጃ ተጎናጸፉ የቪዲዮ ፕሮዳክሽን እና ትክክለኛው የማስተዋወቅ ቴክኒክ

የማህበራዊ ሚዲያ ማስታወቂያዎች

በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ ምርትና አገልግሎቶን ከሁሉም በላቀ ሁኔታ ለታለመለት ሽያጭ እናስተዋውቅሎታለን

የድርጅቶች እና የግለሰቦች ሥልጠና

የድርጅቶች ሥልጠናና ዕድገት ላይ ኢንቨስት ያድርጉ

የኩባንያ ብራንዲንግ፣የአርማ(ሎጎ) ንድፍ(ዲዛይን)

የዲጂታል ግብይት ተሳትፎዎን ከእኛ ጋር ይለኩሱ

በሞዴሎች እና በተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ማስተዋወቅ

በሞዴሎች እና በተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ምርት እና አገልግሎቶን ያስተዋውቁ

ላንዲግ ፔጅ

የእርስዎን ንግድ፣ ምርት እና አገልግሎት ግልጽ እንዲሁም አሳታፊ በሆነ መልኩ የሚያስተዋውቅ የማረፊያ ገጽ እንገነባሎታለን

የድረገጽ ታዋቂነትን ማሳደግ (SEO)

በጎግል የኦላይን መገኘቶን ቀዳሚ ይሁኑ

ጎግል ማስታወቂያ

የሚጎበኞትን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ገዢ ደንበኞች እናደርግሎታለን።

የሶፍትዌር እና የመረጃ ቴክኖሎጂ መፍትሄዎች

በእኛ የሚሰሩት ሶፍትዌሮች እና የመረጃ መፍትሄዎች ውጤታማነትን ለማሳደግ፣ ወጪን ለመቀነስ እና ደንበኞችን ለማርካት የሚበለፅጉ ናቸው።

የመጽሐፍ ሽያጭ

ማናቸውንም ነገር ለማንኛውም ሰው መሸጥ የመቻልን ጥበብ ይካኑ!!

የቪዲዮ ፕሮዳክሽን፤ ለድርጅቶ ተጨባጭ ውጤት ለማግኘት ፈጠራ የታከለባቸው ማስታወቂያዎች እና በየጊዜው እየረቀቀ ከሚመጣው ቴክኖሎጄ ጋር የሚጓዝ አገልግሎ በእርግጥ ያስፈልጎታል::

በላቀ ደረጃ ቪዲዮ ቅንብርን፤ ከስትራቴጂያዊ የማስታወቂያ ቅንብሮች ጋር አዋህዶ በማቅረብ ወደ ሚታወቀውና የማርኬቲን ድርጅት ቁንጮ ወደሆነው ወደ ‹ሱፐር ቡሰት አፕ› እንኳን በደህና መጡ፡፡ የቅርብ ጊዜ ቴክኖሎጂዎችንና ከፍተኛ ክህሎት ያላቸውን  ባለሙያዎችን በማጣመር ልዩ የቪዲዮ ቅንብሮችን ማቅረብ የምንችል በመሆናችን ኩራት ይሰማናል፡፡ ከዚህ አገልግሎታችን በተጨማሪ፤ እንደ ፌስ ቡክ(Facebook)፣ ኢንስታገራም(instagram)፤ ዩቲዩብ(youtube)፣ ቲከቶከና(Tiktok) የመሳሰሉ መድረኮችን የመጠቀም ደረጃና ልምድን በማሳደግና ምርቶችዎን ለገባያ ተደራሾችዎ በአግባቡና በከፍተኛ ብቃት በማስተዋወቅ ረገድ ከማንም በተለየ ሁኔታ እጅግ የተካንን መሆናችንን በደስታ እንገልጽልዎታለን፡፡

ፈጠራ በተሞላበት የተዘጋጁ ቀልብ ሳቢ የሆኑ የማስታወቂያ ፎርማቶች (ስራዎች)

‹ሱፐር ቡስት አፕ› ተደራሾችን በመሳብና ተሳታፊ በማድረግ፤ በዚህም ውጤት በማምጣት  ረገድ፤ ፈጠራ ያለውን ሃይልና አመርቂነት ይገነዘባል፡፡ በጥብቅ ያምንበታልም፡፡ ፈጠራዊ ሥራዎቹ በተለየ ሁኔታ ለደንበኞቻችን ምርቶች ተስማሚ እንዲሆኑ ተደርገው በልዩ ሁኔታ የሚዘጋጁ እና ጠንካራ የግንኙነት ሥልቶች ላይ የሚገነቡ ናቸው፡፡ ሊፈጽሙት ያቀዱት ጊዜን ከግምት ያስገባ ዕቅድ ካለዎት፣ በሱፐር ቡስት አፕ ውስጥ የሚገኙ የብቃት ጥግ ላይ የደረሱት ባለሙያዎቻችንና ስብስባቸው፤ ተቀናጅተው ሕልምዎን ዕውን በማድረግ ማናቸውንም ሁካታና ጫጫታ ዘልቆ በመውጣት ጎልቶ የሚታይ፤ በዚህም ዘላቂ ተጽእኖ የሚያሳድር የማስታወቂያ ፎርማት በማዘጋጀት ረገድ እጅግ የተካንን ነን፡፡ እንደ ሱፐር ቡስት አፕ፣ ዋነኛው ዓላማችን ከሌላው ጋር ተመሳስለንና ተደብቀን የመኖር ጉዳይ አይደለም፡፡ በገበያው ውስጥ መገኘትዎ እንዲታወቅ ከፈለጉ፣ ሱፐር ቡስት አፕ፣ መገኘትዎ እንዲታይ፣ እንዲሰማና እንዲታወቅ ያደርግልዎታል፡፡ ሱፐር ቡስት አፕ እያንዳንዱ የማስታወቂያ አቀራረብ የደንበኞቹን ዋነኛ ግቡን መምታቱን ለማረጋገጥ ይችል ዘንድ፣ ዓይነ ግቡ የማስታወቂያ ጽንሰ አሳቦችን፣ አቀራረቦችን፣ እንዲሁም ዝርዝር ሥራዎችንና ይዘቶችን በመቅረጽ ውጤታማ በሆነ መንገድ ይቆጣጠራል፡፡በተደጋጋሚ ያስመዘገብናቸው ውጤቶች፣ የፈጠራ ሥራዎቻችን በገበያው ውስጥ ከሁሉ የላቁ ናቸው፡፡ ይህን እንደ ማዕዘን ድንጋይ የጠነከረ (አንቱታን ያስገኘልንን) ሥራችንን የምንኮራበት ሲሆን፣ የዚሁ ድንቅ ሥራችን ማሳያ የሆኑ ሥራዎቻችንን ዝርዝር እንደሚከተለው ስናቀርብ በደስታ ነው፡፡

ሥራችን የሚከተሉትን ዘርፎች ያካትታል

  • የቪድዮ ማስታወቂያ ሥራዎችን ወይም ቪዲዬ ፕሮዳክሽንና ፎቶግራፍ ማንሣት:
  • ሞዴልስ እና ኢንፍሎሰር በመጠቀም ማስተዋወቅ
  • የዲጂታል ሚዲያዎች እና መገናኛ ብዙሃን ላይ ማስተዋወቅ Media Planning and Placement
    1. ሶሻል ሚዲያ (social media) ማስታወቂያ
    2. ቴሌቪዥንንና ሬዲዮንን፤ የሚያካትት ማስታቂያዎች
  • የንግድ መለያ ምልክትና ሥያሜ ዝግጅት፣ (logo design and branding)
  • ማስታወቂያዎችን ዲዛይን ማድረግ (graphics design)
  • የኹነቶችንና የማስታወቂያ ሥራዎችን ንድፍ የማዘጋጀት ሥራ event and promotion design….

ቪዲዬ ፕሮዳክሽንና ፎቶግራፍ ማንሣት

ደንበኛ ተኮር እና ከፍተኛ ጥራት ያለው የቪዲዮ ቅንብር ደረጃና የስራ ሂደት ሱፐር ቡስት አፕ አጠቃላይ የሆነ የፕሮዳክሽን አገልግሎት የምንሰጥ ሲሆን ይህም Videography(ተንቃሳቃሽ ምስል)ን እና Photography(ምስል) ያጠቃልላል። እኛ የምንከተለው የ process oriented development ፕሮዳክሽን ለማዘጋጀት የሚፈጀውን ጊዜ፣ ወጪ እና ሪስክ ሚቀንስ ይሆናል። በፕሮፊሽናል ባለሙያ የሚሰራ የፕሮዳክሽን ስራ ድርጅትዎ ትልቅ ትርፍ፣ ብዙ ተመልካችን የሚስብ እና ትክክለኛውን ደንበኛ እና የስራ አጋር እንዲያገኙ ያደርጋል።
አብዛኞቹ የቪዲዮ ፕሮዳክሽንና የፎቶግራፍ ሥራዎች፣ ለተለያዩ የዲጂታል እና ለቴሌቪዥን ለማስታወቂያ የሚጠቅሙ ሲሆን፣ በተለያየ ቦታ እና በስቱዲዮ ውስጥ የሚሰሩ ናቸው፡፡

እኛ የ‹ሱፐር ቡስት አፕ› ባልደረቦች፤ ማናቸውም፣ ብራንድ የራሱ የሆኑ ልዩ ገጽታዎችና መስፈርቶች እንዳሉት እንረዳለን፡፡ ለዚህ ነው፤ የእርስዎን ልዩ ፍላጎት መሰረት ያደረጉና ‹ደንበኛ ተኮር› የሆኑ የቪዲዮ አቅርቦቶችን የምንሰራልዎ፡፡ አሁን ላይ ርስዎ የሚሹት፤ የ‹ብራንድ ማሳወቂያም ሆነ አዲስ ምርት የማስተዋወቅ ተግባር፤ አሊያም ደግሞ ቀልብ ሳቢ ሆነ ዶክመንተሪ ማቀናበርና ማቅረብ፤ የኛ የሙያተኞች ስብስብ ደግሞ፤ ከራስዎ ራእይ ጋርም ሆነ ኢላማ ካደረጓቸው ተደራሾች ፍላጎት ጋር የሚጣጣምና

ተገቢ የሆነ የቪዲዮ ጽንሰ ሃሳብ ለማበልጸግ ከእርስዎም ጋር ተባብሮ ይሰራል፡፡ አስደማሚ የጥራት ምስል ባላቸው ቪዲዎች አማካይነት ሃሳቦችዎ ሁሉ ነፍስ እንዲዘሩ ማድረግ የምንችል በመሆናችን እንኮራለን፡፡

ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸው መገልገያዎች

ሱፐር ቡስት አፕ፤ የቪዲዮ ቅንብር ስራንና አቅርቦትን በተመለከተ፤ በየጊዜው እየረቀቀ ከሚመጣው ቴክኖሎጄ ጋር በፊትአውራሪነት እየተሰለፈ ስራውን የሚያዘምንና የሚያቀላጥፍ ድርጅት ነው፡፡ ከፍተኛ የሆነውን የምርት ወይንም የአቅርቦት እሴትና ውጤት ለማረጋገጥ፤ ጥበባዊ መገልገያዎችንና ፕሮፌሽናል(professional) ካሜራዎች፣ የቅርብ ቴክኖሎጂዎችን ሁሉ እንጠቀማለን፡፡ ስለዚህም ሙያተኞቹ ሆኑ የምናቀርብሎት በጣም ዘመናዊ በሆኑ የቪዲዮ መገልገያ ቴክኖሎጂዎች የታጠቅን በመሆናቸው የቪዲዮ ማስታወቂያዎች ሁሉ ከፍተኛውን የጥራት ደረጃ ተጎናጸፉ ናቸው፡፡  የምስል ጥራት ደረጃቸው ከፍተኛ ከሆኑ ካሜራዎች ጀምሮ እሰከ ተራቀቁ light system የመብራት፣ የድምጽ እና ቪዲዮ ማቀናበሪያ (ኤዲትኒንግ) ሶፍትዌሮችም ድረስ ያሉትን ሁሉ በከፍተኛ ክህሎት በመጠቀም ራእይዎን እውን ለማድረግ የሚያስችለን አቅርቦትና አቅም አለን፡፡ ከኢንዱስትሪዎች እድገቶችና ተለዋዋጭ አቅጣጫዎች ጋር ራሳችንን እያደስንና እያሳደግን ለመጓዝ ባለን ጽናት ምክንያት፤ ከሁሉም የላቁና ልዩ የሆኑ ቪዲዎችን በማቀነባር በተደራሾቻችን ሁሉ ላይ ዘላቂ የሆነ ተጽእኖ ማሳደር የቻልን ነን፡፡

ልዩ የሙያ ክህሎት ያላቸው ባልደረቦች ስብስብና የትብብር ሂደት

ተሰጥኦ ባላቸው ባለሙዎች የተደራጀው የቪዲዮ ፕሮዳክሽን ስራ ቡድናችን የካበተ ልምድና ከፍተኛ ክህሎት ያላቸውን ዳይሬክተሮች፣ የፈጠራ ችሎታቸው እጅግ የዳበረ የሲኒማቶግራፊ ባለሙያዎች፣ ኤዲተሮችና ግራፊክስ ዲዛይነሮችን ያካተተ ከመሆኑም በላይ፤ ባልደረቦቻችን ሁሉ እጅግ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ቪዲዮች ለማቅረብ ሲሉ ሁሌም በጥምረት የሚሰሩ ናቸው፡፡ የኛ ባለሙያዎች ስብስብ እንደ የሙያ ዘርፎቻቸው እጅግ የተካኑ ፕሮፌሽናሎች ናቸው፡፡ የሚፈልጉት ቪዲዮ በሚሰራልዎት ጊዜና በሂደቱ ውስጥ፣ ማለትም የቅድመ ቅንብርን(story board) እቅደ ከማውጣት ጀምሮ እስከ መጨረሻው የኤዲቲንግ ስራ ድረስ፤ ከእርስዎ ጋር በቅርበት በመስራት የምቀናበርልዎ ቪዲዮ፤ ከ‹ብራንድዎ› የመለያ ማንነት ጋር መጣጣሙንና አስፈላጊውን መልእክት በቅጡ ማስተላለፉን፤ በዚህም አማካይነት ውጤት ማምጣት መቻሉን ለማረጋገጥ እስከመጨረሻው ተግተን እንሰራለን፡፡ ለሁሉም ክፍት በሆነ ግልጽ የትብብር መንፈስ የምናምን በመሆናችን ደንበኞቻችንም ቢሆኑ የሂደቱ ሁሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ እናደርጋለን፤ ምክንያቱም ደንበኞቻችን የሚሰጡን አስተያየት ሁሉ ለኛ ትልቅ ግብአት ከመሆኑም በላይ፤ የመጨረሻው አላማችንና ግባችን፤ የእርስዎ የደንበኛቻችን እርካታ ብቻ ነው፡፡

አርት ዳይሬክቲግ

ሁለንተናዊ የሆኑ የማስታወቂያ ስራዎች፤ ተገቢና ተመጣጣኝ የሆነ ማኔጅመንትና፤ Digital ገጽታዎችን ሁሌም ወደላይ የማሳደግ ብርቱ ጥረት እንደሚያስፈልጋቸው ቀድመን የተረዳን ነን፡፡ ስለዚህ ማናቸውንም የማስታወቂያዎችዎን ገጽታዎች ሁሉ፤ ከመጀመሪያው የእቅድና የስትራቴጂ ንድፍ ጀምሮ እስከ ተግባራዊነቱነ ፍጻሜ ድረስ እያንዳንዱን ጥቃቅን እንቅስቃሴ እንከታተላለን፤ እንቆጣጠራለን፡፡ ያለማቋረጥ ቁልፍ የሆኑ ሂደቶችንና አፈጻጸሞችን በመተንተን፤

ኢንፎርሜሽን ላይ የተመሰረቱ ማሻሻያዎችን እናድረጋለን፡፡ በዚህም የእርስዎ ማስታወቂያዎች የመጨረሻውን ተፈላጊ ውጤት ማምጣት መቻላቸውንና አለመቻላቸውን እንቆጣጠራለን፡፡

አጠቃላይ የማስታወቂያ እና የውጤቶች ሪፖርት ማኔጅመንት (Digital/Social Media Marketing Anylisis)

በ‹ሱፐር ቡስት አፕ› ውስጥ፤ ዋናው ትኩረታችን፤ ልዩ የሆነ የቪዲዮ ቅንብርና ለብራንድዎ ተጨባጭ ውጤት የሚያስገኙ የማስታወቂያ አገልግሎቶችን ማቅረብ ነው፡፡ ባለን የፈጠራ እምቅ ሃይልና ችሎታ፤ እንዲሁም የእርስዎን የፕሮፌሽናል ደረጃ ለማሳደግና፤ በዚህም እርስዎን ስኬታማ ለማድረግ የምናደርገው ጥረት አመርቂ ውጤት እንሚያስገኝሎት እርግጠኛ ነን፡፡

ሁለንተናዊ የሆኑ የማስታወቂያ ስራዎች፤ ተገቢና ተመጣጣኝ የሆነ ማኔጅመንትና፤ ገጽታዎችን ሁሌም ወደላይ የማሳደግ ብርቱ ጥረት እንደሚያስፈልጋቸው ቀድመን የተረዳን ነን፡፡ ስለዚህ ማናቸውንም የማስታወቂያዎችዎን ገጽታዎች ሁሉ፤ ከመጀመሪያው የእቅድና የስትራቴጂ ንድፍ ጀምሮ እስከ ተግባራዊነቱነ ፍጻሜ ድረስ እያንዳንዱን ጥቃቅን እንቅስቃሴ እንከታተላለን፤ እንቆጣጠራለን፡፡

ያለማቋረጥ ቁልፍ የሆኑ ሂደቶችንና አፈጻጸሞችን በመተንተን፤ ኢንፎርሜሽን ላይ የተመሰረቱ ማሻሻያዎችን እናድረጋለን፡፡ በዚህም የእርስዎ ማስታወቂያዎች የመጨረሻውን ተፈላጊ ውጤት ማምጣት መቻላቸውንና አለመቻላቸውን እንቆጣጠራለን፡፡

የማስታወቂያ ዘመቻዎችዎን አፈጸጻምና ውጤትም ከስር ስር እንከታተላለን፡፡ እንደ ‹conversion፣ ‹click through rate› እና ‹impressions› ያሉ ሜትሪክሶችን በመተንተን፤ ስለተደራሾችዎ ባህርይም ሆነ ስለማስታወቂያ ዘመቻው ውጤታማነት ዋጋ ያላቸው ግንዛቤዎችን እናዳብራለን፡፡

ይህ ኢንፎርሜሽን ተኮር የሆነ አቀራረብ፤ በመረጃና በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ውሳኔዎችን እንድንወስንና፤ ከፍተኛ ውጤት የሚያስገኙ ቀጣይ ዘመቻዎችን እንድንቀይስ ያስችለናል፡፡‐‑የማስታወቂያ ዘመቻዎችዎ ሳያቋርጡ እየተሻሻሉ እንዲሄዱና ሁሌም አመርቂ ውጤት የሚያስገኙ እንዲሆኑ ለማድረግ በጽናት የቆምን ነን፡፡

በማያቋርጥ ክትትልና ትንተና አማካይነት፤ መሻሻል የታየበቻውን ገጽታዎች እየለየንና ሁሌም የበለጠ እንዲሆኑ በማስቻል፤ ከንግድ ስራዎ ከፍተኛ የሆነ ተመላሽ ገቢ እንዲያገኙ በከፍተኛ ደረጃ እንሰራለን፡፡

የምንቀርባቸው ሪፖርቶችም፤ የስኬትዎን ደረጃ ለመለካትና ወደፊት የሚያኪያሄዷቸውን የማስታወቂ ዘመቻዎች በተመለከተ በእውቀት ላይ ተመሰረተ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡

ቴሌቪዥንንና ሬዲዮንን፤ የሚያካትት ማስታቂያዎች

ሱፐር ቡስት አፕ፣ ደንበኞቹን ወክሎ በተአማኒ የሚዲያ አውታሮች ላይ ማስታወቂያ ማስነገር የሚያስችለው ሙሉ ዕውቅና አለው፡፡ ከሁሉም ሚዲያዎች ጋር በጣም ጥሩ ግንኙነት ያለው በመሆኑም፣ ጥሩ ዋጋዎችንና የመሥሪያ ቦታዎችን ለማግኘት የሚያስችሉ ድርድሮችን የማድረግ፣ እንዲሁም ሚዲያዎች ውስጥ ልዩ ዕድሎች ሲኖሩ መረጃውን ቀድሞ የማግኘት አቅም አለው፡፡

የሱፐር ቡስት አፕ ባለሙያዎች ቡድን የደንበኛን የሸመታ ዓውድ በሚመለከት የጠለቀ እውቀት ያለው ነው፡፡ የሕዝብን ስብጥር፣ እንዲሁም የደንበኞችን የማየት፣ የማንበብ እና የማዳመጥ ልማዶችን ከግምት ያስገባ ትንታኔና ግምገማ ካደረገ በኋላ፣ የተሻለውን የሚዲያ አማራጭ ይጠቁማል፡፡

የሚዲያ መርሐ ግብር ዕቅድ ዝግጅታችን፣ በተአማኒ ሚዲያዎች ላይ መረጃው እንዲደርሳቸው ለሚፈለጉ አካላት የሚነገርበት ተገቢና ትክክለኛ ሁኔታ ላይ በመመሥረት የሚካሄድ ነው፡፡

 

ድርጅቶች ሞዴሎችን ወይም ተፅዕኖፈጣሪዎችን በመጠቀም በዲጂታል/ሶሻል ሚዲያ ማስተዋወቅ፡፡ ሶሻል ሚዲያዎች ልክ እንደ ኢንስታግራም፤ ቲክቶክ፤ ዩቱዩብ አንዲሁም ቴሌቪዥንንና ሬዲዮንን፤ ሞዴሎችን እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን በመጠቀም
ለማስተዋወቅ አሪፍ አማራጮች ናቸው፡፡ በጣም ማራኪ፣ ለዕይታ ሚስቡ እና አይረሴ ምስሎችን እና ቪድዮችን በመስራት ለተፈለገው ተመልካች ማድረስ ይቻላል፡፡

የምርት ክፍል ቡድናችን ከተለመደው ወጣ ያሉ የምርት መለያዎችንና ምልክቶችን በመፍጠር ረገድ ዝናን ያተረፈ ነን፡፡

ማስታወቂያዎችን ዲዛይን ማድረግ

ከፍተኛ ውጤቶችን የሚያስመዘግቡ የገበያ (የንግድ) ሥልቶችን በመቅረጽ፣አነስተኛ የሚባል የማስታወቂያ ወጪ ብቻ እንዲያወጡ በማድረግ እንዲሁም የሚፈለገውን ዓላማከማሳካት አንጻር አዎንታዊ ውጤቶች እንዲያገኙ በማድረግ ደንበኞቻችንን እናግዛለን፡፡

የኹነቶችንና (ኢግዚብሽን /ባዛር) የማስታወቂያ ሥራዎችን ንድፍ የማዘጋጀት ሥራ

በ Super boost up የተካነውን የማስታወቂያ ንድፋችንን በመጠቀም ብቻ ሊረሱት የማይችሉትን ዝግዘጅት እና የተለያዩ ማስተወቂያዎችን ማዘጋጀት ይችላሉ። በዘርፉ የተካኑት ባለሞያዎቻችን በአንድ እይታ ብቻ ትልቅ ተጽእኖ መፍጠር የሚችሉ አስደናቂ መልዕክቶችን ያዘጋጁሎታል፤ ሰራተኞቻችንም ለእያንዳንዱ ትናንሽ ነገር ትኩረት ስለሚሰጡ እና በትጋት ስለሚሰሩ ለተደራሽ ምቹ በሆነ መንገድ መልዕክትዎ ይደርሳል። የእኛን አገልግሎት በመጠቀም ተከታይዎትን ያሳድጉ፣ የንግድዎን መልእክት ተደራሽነትም ያስፉ። ማራኪ ውጥኖችን ለዓይን በሚማርኩ የማስተዋወቂያ ቁሳቁሶች ተጠቅመን በዲጂታል ግብይት እንቅስቃሴዎ አዲስ ከፍታ ላይ እናደርስዎታለን። እርሶ ብቻ ጉዳዩን በእኛ ይጣሉት!

የእኛ ሥራ

የማስታወቂያ አገልግሎቶች፣ የሚዲያ ዕቅድና የውክል ማስታወቂያ ሥራዎች፣ የቴሌቪዥንና የሚዲያ ፕሮዳክሽን፣ የሕዝብ ግንኙነት፣ ኹነቶችን (ዝግጅቶችን) ማካሄድ፣ የጠቋሚ (መረጃ ሰጪ) ማስታወቂያ ምልክቶች፣ግራፊክ ዲዛይን፣ ፎቶግራፍ ማንሣት እና የኪነጥበብ (አርት) ዳይሬክቲንግ ሥራዎች፡፡

ተልዕኮአችን

የድርጅታችን ተልዕኮ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዕድሎችን ወይም አቅሞችን በመጠቀም፣ ጥራት ያላቸው የግብይት መፍትሔዎችን በማቅረብ ረገድ ከፍተኛ ብቃትን መጎናጸፍ፡፡

ተልዕኮአችን –የድርጅታችን ተልዕኮ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዕድሎችን ወይም አቅሞችን በመጠቀም፣ ጥራት ያላቸው የግብይት መፍትሔዎችን በማቅረብ ረገድ ከፍተኛ ብቃትን መጎናጸፍ፡፡ 

ተጨማሪ አገልግሎቶች –የፈጠራ አሳቦችና የኪነጥበብ (አርት) ሥራዎች፣ የንግድ ሥያሜ ሥልቶችና አገልግሎቶች፣ የግብይትና የማማከር አገልግሎቶች፣ የምርት ማስተዋወቅ ሥራዎችን ማቀድና መተግበር፣

amAM