SuperBootsUp

Edit Content

ድህረ-ገፅ ማበልፀግ

ንግዶን የሚያሳድግ ውጤታማ እና አስተማማኝ ድህረ ገፅ ከኛ ያገኛሉ

የቪዲዮ ፕሮዳክሽን

ከፍተኛውን የጥራት ደረጃ ተጎናጸፉ የቪዲዮ ፕሮዳክሽን እና ትክክለኛው የማስተዋወቅ ቴክኒክ

የማህበራዊ ሚዲያ ማስታወቂያዎች

በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ ምርትና አገልግሎቶን ከሁሉም በላቀ ሁኔታ ለታለመለት ሽያጭ እናስተዋውቅሎታለን

የድርጅቶች እና የግለሰቦች ሥልጠና

የድርጅቶች ሥልጠናና ዕድገት ላይ ኢንቨስት ያድርጉ

የኩባንያ ብራንዲንግ፣የአርማ(ሎጎ) ንድፍ(ዲዛይን)

የዲጂታል ግብይት ተሳትፎዎን ከእኛ ጋር ይለኩሱ

በሞዴሎች እና በተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ማስተዋወቅ

በሞዴሎች እና በተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ምርት እና አገልግሎቶን ያስተዋውቁ

ላንዲግ ፔጅ

የእርስዎን ንግድ፣ ምርት እና አገልግሎት ግልጽ እንዲሁም አሳታፊ በሆነ መልኩ የሚያስተዋውቅ የማረፊያ ገጽ እንገነባሎታለን

የድረገጽ ታዋቂነትን ማሳደግ (SEO)

በጎግል የኦላይን መገኘቶን ቀዳሚ ይሁኑ

ጎግል ማስታወቂያ

የሚጎበኞትን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ገዢ ደንበኞች እናደርግሎታለን።

የሶፍትዌር እና የመረጃ ቴክኖሎጂ መፍትሄዎች

በእኛ የሚሰሩት ሶፍትዌሮች እና የመረጃ መፍትሄዎች ውጤታማነትን ለማሳደግ፣ ወጪን ለመቀነስ እና ደንበኞችን ለማርካት የሚበለፅጉ ናቸው።

የመጽሐፍ ሽያጭ

ማናቸውንም ነገር ለማንኛውም ሰው መሸጥ የመቻልን ጥበብ ይካኑ!!

ከወር እስከ ወር ከ20-250 በፌስቡክ ማስታወቂያ “የሽያጭ መሪዎችን” ያግኙ

በየዕለቱ ኢትዩጵያ ውስጥ 7.05 ሚሊዮን የሚሆኑ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የፌስቡክ ገጻቸውን ይመለከታሉ፡፡ በዚህ ግዙፍ የሆነ የመገናኛ መስመር በኩል ንግድዎንና ድርጅትዎን ማስተዋወቅ ለነገ የሚባል አይደለም፡፡

ፌስቡክ በየዕለቱ በቋሚነት የሚጠቀሙ 2.09 ቢሊዮን ደንበኞች አሉት፡፡ በቀን በአማካይ 4 ቢሊዮን የላይክ ምልክቶች ተጠቃሚዎቹ ይለዋወጣሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሰባት ሚሊዬን የሚሆኑት ቋሚ ተጠቃሚዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ናቸው፡፡ እውነታው ይህ ነው፡፡ የፌስቡክ ጥቅም ሰዎችን ከማጎዳኘት ከተሻገረ ቆይቷል፡፡እስኳሁን ፌስቡክን ለግብይትዎ፣ ለንግድዎ በሚጠቀቅም መልኩ መገልገል ካልጀመሩ ምን ያክል ንቁና ምርጥ ደንበኞችን ለተፎካካሪዎችዎ አሳልፈው እየሰጡ እንደሆነ ያስቡት፡፡የማስታወቂያ አቅምዎንና ጉልበትዎን ሁሉ በአረጀ በአፈጀ የማስተዋወቅ ብልሃት በከንቱ እያባከኑ መሆኑን መገንዘብ አለብዎት፡፡

እንደ ጎርፍ በሚያጥለቀልቅ ለግዢ ዝግጁ የሆነ የግብይት ማዕበል እንዲወሰዱ ልናደርግዎት እንፈልጋለን፡፡

እንደ ፌስቡክ የግብይትና የንግድ ማስተዋወቅ ምቹነት ያላቸው የቴክኖሌጂ አማራጮች ጥቂት ናቸው፡፡ ፌስ በቀላሉ ሊደርሱባቸው የሚችሏቸው ሰባት ሚሊዮን የደንበኞ አማራጮችን ብቻ አያቀብለዎትም፡፡ የማስታወቂያ ወጭዎትንም ወደ ዜሮ ያወርድለዎታል፡፡ ይህ ትክክለኛውን መንገድ ሲከተሉ ነው ፤ ካልሆነ ልክ እንደቁማር ነው (casino gambling) ፡፡

እኛ ከዚህ ሁሉ መንጋ የፌስቡክ ሰራዊት በዕድሜና በጾታ እየለየን የእርስዎን ተመራጭ (ትክክለኛ ምርቶን ፈላጊ) ደንበኞች እንዲያማልሉ ዕገዛ ደርጉለዎታል፡፡
የሚገኙበትን ቦታ (አገር ውስጥ ወይስ ከአገር ውጪ)፣ የሚከተሏቸውን ገጾች፣ እና ዝንባሌያቸውን እየለየን ወደትክክከለኛው ደንበኛዎ እንዲደርሱ እንረዳዎታለን፡፡ሌሎች ተጨማሪ ፈጠራዎችን (Algorism) በመጠቀም የእርስዎን መኖር የማያውቁ የእርስዎን ምርት ፈላጊዎች ጋር እናደርሶታለን፡፡

በፌስቡክ ንግድዎን ያሳግጉ

ፌስቡክ ላይ ማስተዋወቅ ሲጀምሩ በቀላሉ የሚደረስባቸው የበሰሉና የሚያስጎመጁ ፍራፍሬዎች ማሳ ውስጥ እንደተገኙ ይቁጠሩት፡፡ትኩረትዎን በዋነኞቹ የድርጅትዎ ተፈላጊ ደንበኞች ላይ እንዲያነጣጥር ማድረግ ይችላሉ፡፡ ዘርፉን አሰራሩን እንደማያውቅ ሰው ድንገት ዘው ብለው ሲገቡ ብዙ ነገር ሊደነጋገርዎ እንደሚችል ይገባናል፡፡እኛ ግን ከዚህ በፊት ለማስታዊያ ያወጡ ከነበሩት አንጻር ሽርፍራፊ ሊባል በሚችል ወጪ ይህንን ታላቅ ጥበብ እንዲካኑበት ልንረዳዎት ዝግጁ ናቸው፡፡ የፌስቡክ ማስታወቂያ ተጠቃሚዎች ለሚያወጧት ለእያንዳንዷ አንድ ብር ሦስት ብር እያጋበሱ መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡በዚህ ላይ ፌስቡክ ላይ ለመስታወቂያ የሚወጣው ወጪ ከሌላው አንጻር በእጅጉ ዝቅተኛ ነው፡፡ንባብዎን ይቀጥሉና ማስታወቂያዎ በራሱ እስኪቆም ድረስ በቀላል መንገድ ምን እንደምናደርግልዎ እንድናሳይወት ይፍቀዱልን…

ሶሻል ሚዲያ ማስታወቂያ

በዛሬው ዲጂታላዊ(digital) አለም ውስጥ፤ ሶሻል ሚዲያ (social media) መድረኮች ማስታወቂ በማሰራጨትና ለብዙ የገባያ ኢላማዎች ተደራሽ በመሆን ረገድ ብርቱና ፍቱን መገልገያዎች ሆነዋል፡፡

የፌስቡክና የኢንስታገራም ማስታወቂያዎች—እነዚህ ሁለቱ በቢሊዮኖች ሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ስላሏቸው፤ የገባያ ተደራሾችን በስፋት ለማገግኘት ሰፊ እድል የሚሰጡ ናቸው፡፡የኛ የባለሙያዎች ስብስብ፤ የቪዲዮና የፎቶ ማስታወቂያ የመሳሰሉትን ቴክኒኮች ከማራኪ ትረካ ስልት ጋር በመጠቀም ከተደራሸችዎ ፍለጎትና ልብ ጋር አብሮ የሚነዝርና ቀልብ ሳቢ የሆነ የማስታወቂያ ዘመቻ እንሰራልን፡፡

የቲክቶክ ማስታወቂያ—ወጣት የሆኑ ተደራሾችን ስርጭትን በሚመለከት ቲክ ቶክ ሁነኛና ዝነኛ መድረክ ለመሆን በቅቷል፡፡ እኛም የዚህን መድረክ ተጠቃሚዎች ቀልብ የሚስብ ዝነኛ የማስታወቂያ ዘመቻ ማካሄድ እንዲቻል፤ የዚህን መድረክ አቅርቦቶች አንጠፍጥፎ ለመጠቀም የሚስችሉንን ስልቶች ሁሉ በጥንቃቄ ነድፈናል፡፡

የዩቲዩብ ማስታወቂ-ያ—ዩ ቲዩብ ለቪዲዮ ቅንብርና ማስታወቂያ አይነተኛው መድረክ ሲሆን፤የኛ ባለሙያዎች ቡድን፤ ከመድረኩ ገጽታዎችና ባህርያት ጋር አብረው የሚሄዱና ተለያዩ የሆኑ የማስታወቂያ ስልቶችን ይነድፋል፡፡ የ‹ፕሪ ሮል›(pre roll) ማስታዎቂያዎችንም ሆነ ማስታወቂዎችን እንዲሁም የገጽ አናት ላይ ‹ደባል ቪዲዎችን›፤ ወዘተ በሚመለከት የምናቀነባብራቸውን የዬ ቲዩብ ማስታወቂዎቻችንን፤ ከተመልካቾች ፍለጎት ጋር አብረው የሚሔዱና ተግባራዊ ደንበኞችን በፍጥነት ለማፍራት የሚያስችሉ እንዲሆኑ ማድረግ ችለናል፡፡

ከነዚህ መድረኮች በተጨማሪ፤ ብራንድዎን ለማስተዋወቅ የሚያስችሉ ሌሎች ተጓዳኝ መድረኮችንም እያሰስን በጥቅም ላይ እናውላለን፡፡ ይህን የምንከውነውም የነደፍነውን ስትራቴጂ ሁሉ ከአዲስ አይነቶቹ መድረኮች ጋር እንዲጣጣሙ ለማድረግ እንደ ተጠቃሚዎች ዴሞግራፊ፣ የባህርይና የምርጫ አዝማሚያና፤ እንዲሁም ማስታወቂያ የመልቀቅ አማራጮችን በማጤንና ስልት በመቀየስ ነው፡፡ ምክንያቱም የመጨረሻው አላማችን የእርስዎ ብራንድ በተገቢው ደረጃ መተዋወቁንና ውጤት ማምጣቱን ማረጋገጥ ነው፡፡

የዲጂታል ሚዲያዎች እና መገናኛ ብዙሃን ላይ ማስተዋወቅ

እንደ ፌስ ቡክ፣ ኢንስታገራም፣ ዩ ቲዩብና ቲክቶክ ካሉ መድረኮች በተጨማሪ፤ ሌሎች አይነቶችንም በማካተት መድረከ- ብዙ የሆነ ማስታወቂያ የማካሄድ አስፈላጊነትን እንረዳለን፡፡ስለዚህ፤ የማስታወቂያወቻችንን ተደራሽነት ለማስፋትና አንደምታቸውን ለማሳደግ፤ ሌሎች መድረኮችንና ማስተላለፊዎችንም ዘወትር እያሰስን እንጠቀማለን፡፡ 

ይህም፤ ነባር የሆኑ እንደ ቴሌቪዥንንና ሬዲዮንን፤ የሚያካትት ነው፡፡ ስትራቴጂያዊ በሆነ መንገድ ተገቢዎቹን ሚዲያዎች በመምረጥና በማጣመር፤ የእርስዎ የማስታወቂያ መልክቶች ኢላማ ወደአደረጓቸው ተደራሾች  መድረሳቸውንና ብራንድዎም ልዩና ጎልቶ የሚታወቅ መሆኑን በሚያረጋግጥ መንገድ ስራችንን እንሰራለን፡፡

እኛ እምንሰራው

ሰዎች የኦንላይን ቢዝነስ
እንዲያደራጁ መርዳት ነው

amAM