SuperBootsUp

Edit Content

ድህረ-ገፅ ማበልፀግ

ንግዶን የሚያሳድግ ውጤታማ እና አስተማማኝ ድህረ ገፅ ከኛ ያገኛሉ

የቪዲዮ ፕሮዳክሽን

ከፍተኛውን የጥራት ደረጃ ተጎናጸፉ የቪዲዮ ፕሮዳክሽን እና ትክክለኛው የማስተዋወቅ ቴክኒክ

የማህበራዊ ሚዲያ ማስታወቂያዎች

በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ ምርትና አገልግሎቶን ከሁሉም በላቀ ሁኔታ ለታለመለት ሽያጭ እናስተዋውቅሎታለን

የድርጅቶች እና የግለሰቦች ሥልጠና

የድርጅቶች ሥልጠናና ዕድገት ላይ ኢንቨስት ያድርጉ

የኩባንያ ብራንዲንግ፣የአርማ(ሎጎ) ንድፍ(ዲዛይን)

የዲጂታል ግብይት ተሳትፎዎን ከእኛ ጋር ይለኩሱ

በሞዴሎች እና በተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ማስተዋወቅ

በሞዴሎች እና በተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ምርት እና አገልግሎቶን ያስተዋውቁ

ላንዲግ ፔጅ

የእርስዎን ንግድ፣ ምርት እና አገልግሎት ግልጽ እንዲሁም አሳታፊ በሆነ መልኩ የሚያስተዋውቅ የማረፊያ ገጽ እንገነባሎታለን

የድረገጽ ታዋቂነትን ማሳደግ (SEO)

በጎግል የኦላይን መገኘቶን ቀዳሚ ይሁኑ

ጎግል ማስታወቂያ

የሚጎበኞትን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ገዢ ደንበኞች እናደርግሎታለን።

የሶፍትዌር እና የመረጃ ቴክኖሎጂ መፍትሄዎች

በእኛ የሚሰሩት ሶፍትዌሮች እና የመረጃ መፍትሄዎች ውጤታማነትን ለማሳደግ፣ ወጪን ለመቀነስ እና ደንበኞችን ለማርካት የሚበለፅጉ ናቸው።

የመጽሐፍ ሽያጭ

ማናቸውንም ነገር ለማንኛውም ሰው መሸጥ የመቻልን ጥበብ ይካኑ!!

ሱፐር ቡስት አፕ የድርጅቶች እና የግለሰቦች ሥልጠና

የድርጅት ሥልጠናና ዕድገት ላይ ኢንቨስት ያድርጉ፡፡

በየጊዜው በሚቀያየር ዓለም ውስጥ፣ሠራተኞችዎን ክኅሎትና እውቀት ማሳደጉ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ በድርጅትዎ ውስጥ ያሉ የሠራተኛ ቡድኖች፣ የሚገጥማቸውን ማንኛውንም ሁኔታ ተላምደው መሥራት መቻል አለባቸው፡፡

ድርጅቶች በየትኛውም ዓይነት የሥራ ዘርፍ ቢሠማሩም፣ ድርጅታዊ ሥልጠና፣ ኩባንያዎች ስኬታማ እንዲሆኑ የሚያደርጓቸው የትምህርትና እድገት ሥልት አካል ነው፡፡ በእውቀት ሽግግር አማካይነት፣ ድርጅቶች ከተቀናቃኞቻቸው አንጻር ያላቸውን ብልጫ ማሳደግና ውጤታማነታቸውን መጨመር ይችላሉ፡፡

ድርጃታዊ ሥልጠና የሚያገኙ ሠራተኞች፣ በሙያዊም ሆነ በግላዊ ሕይወታቸው ዕድገት ያሳያሉ፡፡ በዚህ ሂደት፣ የአስተሳሰብ አድማሳቸውን እንዲያሰፉ የሚበረታቱ ሲሆን፣ ይህም የንግድ ሥራ ዕድገትን ያስከትላል፡፡

እያንዳንዱ ድርጅት በንግድ ሥራው ስኬታማ መሆን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፣ ትልልቆችም ሆኑ ትንንሽ ድርጅቶች፣ ድርጅታዊ ሥልጠና የኩባንያቸውን እድገትና ደኅንነት ከማረጋገጥ አንጻር የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንትን ያህል ጠቀሜታ ያለው መሆኑን መረዳት አለባቸው፡፡

የግል እድገትና መጎልበት የሠራተኞችዎን ቡድን ዕምቅ አቅማቸውን እንዲጠቀሙ ከማስቻል አንጻር ምን ዕገዛ ሊያደርግ እንደሚችል ለማወቅና ለድርጅታዊ ሥልጠና ከሚያፈስሱት መዋዕለ ንዋይ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ ለመሆን፣ ከሱፐር ቡስት አፕ ጋር ይገናኙ፡፡ ስኬታማ የሥልጠና ትምህርቶች (courses)፣ የአንድን ኩባንያ የንግድ ሥራ ዓላማዎች ለመደገፍ የሚጠቅሙ መሣሪያዎችንና እውቀቶችን ለሠራተኞች የሚያስታጥቁ ናቸው፡፡

የድርጅቶች እና የግለሰቦች ሥልጠና

የሱፐር ቡስት አፕ ድርጅታዊ የክኅሎት ሥልጠናዎች በአብዛኛው በአግባቡ የተዋቀሩና መደበኛ ናቸው፡፡ የሚቀርቡት ሥልጠናዎች ይዘት ቀድሞ የተዘጋጀ እና በመርሐ ግብር የሚቀርብ ነው፡፡ የክኅሎት ሽግግር የሚደረግባቸው ጉዳዮች እንደየ ሁኔታው፣ ቴክኒካዊ፣ ድርጅታዊ፣ ወይም ዓውዳዊ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ድርጅታዊ ሥልጠና እንደየ ሁኔታው ልዩ የሚሆንበት ምክንያት፣ ጠቅላላው ድርጅት የሚቀስመው ልምድ ተመሣሣይ በመሆኑ ነው፡፡

የድርጅታዊ ሥልጠናን አስፈላጊነት መረዳት፣ ስኬታማ ንግድን ከማረጋገጥ አንጻር እጅግ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ 

ለጀማሪዎች፣ ሠራተኞችን ማጎልበት አጠቃላይ ድርጅቱን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡ ብዙዎቹ የተቀጠሩም ሆኑ ገና ለመቀጠር በሂደት ላይ ያሉ ሠራተኞች፣ ሙያዊ ዕድገትንና ሥልጠናን እንደሚፈልጉ ይናገራሉ፡፡ በመጨረሻም፣ ሰዎች ለሥራቸው ብቁ የመሆን ስሜት እንዲሰማቸውና በሥራቸው ምን እንደሚጠበቅባቸው ማወቅ የሚፈልጉ ሲሆን፣ ከዚህ አንጻርም፣ የሱፐር ቡስት አፕ ድርጅታዊ ሥልጠና ትልቅ ዕገዛ ይደርጋል፡፡

ድርጅቶች የሥራ ባሕላቸውን እና ባሕሪያቸውን እንዲቀይሩና በከፍተኛ ደረጃ እንዲያጠናክሩ እንረዳቸዋለን፡፡ እያንዳንዱ ባለሙያ እና አለቃው፣ ከተቻለም እያንዳንዱ የኩባንያው ሠራተኛ፣ የሚያስፈልገውን የእድገት ዓይኘትና ደረጃ የምንረዳበት የተረጋገጠና አስተማማኝ መንገድ ፈጥረናል፡፡ እነዚህን ፍላጎቶች (ክፍተቶች) ለመሙላት የተለያዩ ዘዴዎችን ተጠቅመን የክኅሎትም ሆነ የአሠራር ሥልጠና እንሰጣለን፡፡

የሱፐር ቡስት አፕ ድርጅታዊ ሥልጠና ጥቅሞች

  • የሱፐር ቡስት አፕ ድርጅታዊ ሥልጠና በተቋም ደረጃ እውቀት መፈጠሩን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ድርጅታዊ ሥልጠናን፣ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ካለው ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እስካለው እያንዳንዱ የኩባንያው ሠራተኛ ድረስ አዲስ ነገርን የሚጨብጥበት ሁሉን አቀፍ የተቋሙ የእውቀት መዋቅር አድርገው ያስቡት፡፡ ሠራተኞቹ ያገኙትን እውቀት በድርጅቱ ውስጥ ባላቸው ሥራ ላይ በመተግበር ለሌሎች የሚያጋሩት ሲሆን፣ ይህም ልምዳቸውን ለማሻሻል ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡ እውቀቱ በተግባር ከተተረጎመ በኋላ ከግለሰብ እውቀትነት ወደ ድርጅታዊ ማኀረበረሰብ እውቀትነት (ባሕልነት) ይሸጋገራል፡፡ ድርጅቶች በየጊዜው ከሚለዋወጥ ከባቢያዊ ሁኔታ ጋር መላመድና የረጅም ጊዜ ስኬት ማስመዝገብ የሚችሉት በዚህ መንገድ ነው፡፡ 

  • የሱፐር ቡስት አፕ ድርጅታዊ ሥልጠና፣ ንቁ ተሳትፎና ትብብርን የሚያበረታታ ነው፡፡ አሳታፊ የሆነ የሥራ ቦታ ላይ፣ ሠራተኞች ተቋማቸው ያሉበትን ችግሮች ለይቶ እንዲያውቅ እና ወደ መፍትሔዎቹም እንዲደርስ ያገኙትን ዕድል ሁሉ መጠቀም ይፈልጋሉ፡፡ በመጨረሻም ሠራተኞች ክኅሎቶቻቸውን ለማሳደግ፣ ብሎም የሥራ ክንውናቸውን ለማሻሻል እነዚህን አጋጣሚዎች ይጠቀማሉ፡፡ ሠራተኞችዎ ለድርጅትዎ ርዕይ እና ተልእኮ አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ ከፈለጉ፣ የክኅሎት ብቃታቸውን በመጨመር ረገድ ኢንቨስት ማድረግዎ ዓላማዎን ለማሳካት ጥረት እንዲያደርጉ ያግዛቸዋል፡፡ በተጨማሪም፣ ሥልጠናው ከሥራቸው ጋር የሚሄድና ክኅሎታቸው ላይ የሚያተኩር ከሆነ፣ ኩባንያውም ሠራተኞቹም በጋራ የሚያተርፉበት የሁለት ወገን ተጠቃሚነትን የሚያስገኝ ነው፡፡ ይህ አካሄድ፣ ሠራተኞች ሥራቸው ላይ ከልባቸው እንዲሳተፉና እርካታ እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል፤ በዚህም የሥራ አፈጻጸማቸውን የሚያሻሽሉ ሲሆን፣ ሱፐር ቡስት አፕም ይህን ለማገዝ ከጎናቸው ይገኛል፡፡

  • የሱፐር ቡስት አፕ ድርጅታዊ ሥልጠና፣ ሂደቶቹን የሚፈጥረው፣ ኢንቨስት እያደረገና (መዋዕለ ነዋዩን እያፈሰሰ) እየመራ ካለው የድርጅቱ አስተዳደር፣በተግባር በሥራው ላይ ሆነው ተግዳሮቶችን እየተጋፈጡ ካሉት አካላት ተነሥቶ ነው፡፡ በእርግጥ፣ በሱፐር ቡስት አፕ የሥልጠና ውጤቶች፣ አስፈላጊ የሆኑትን እና ያልሆኑትን ለይቶ ለማወቅና ለማደራጀት የሚረዳ መዋቅር ማዘጋጀት የሚጠበቅ ነው፡፡ ይህ አካሄድ፣ ነገሮች በቀላሉና በተስተካከለ ሁኔታ የሚሠሩባቸውን ሥርዓቶች የሚጠቁም ጭምር ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜም፣ ይህ መርሐ ግብር፣ ሥራ አስኪያጁ ወይም ሌላ የድርጅቱ ባልደረባ፣ የተደራጀ አሠራር ውስጥ መግባት እና ማስቀጠል የሚያስችል የግል ወይም የቡድን የተግባራዊ እርምጃ ዕቅድ እንዲያዘጋጁ ያግዛል፡፡ ስለዚህ የሱፐር ቡስት አፕ ድርጅታዊ ሥልጠና፣ በድርጅትዎ ውስጥ ለውጥ የሚያቀጣጥል መሣሪያ ሊሆን ይችላል፡፡

የምናቀርባቸው ሥልጠናዎች፣ Personal growth and development ፣ግቦችና ዕቅዶችን የማስቀመጥ እና መተግበር ክህሎት፣ የሽያጭ ሥልጠናዎችን፣ የእንግዳ ተቀባይ ባለሙያ(Receptionist training)ሥልጠናዎችን፣ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ሥልጠናዎችን ያካተቱ ናቸው፡፡

ግለሰቦች የራሳቸውን አቅም ሚያሳድግጉበት እና ሚያጎለብቱበትሥልጠና

ለግለሰቦች ምንሰጣቸው ሥልጠናዎች፣ Personal growth and development፣ ግብ እና ዕቅድ የማስቀመጥ እና መተግበር ክህሎት፣ የሽያጭ ሰራተኞች ሥልጠና እንዲሁም ሌሎች በርካታ ሥልጠናዎችን ያካተቱ ሲሆን፣ እነዚህን እና በርካታ ሥልጠናዎችም LEARNING MANAGEMENT SYSTEM (LMS) በሚባለው መድረካችን ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ ይህ መድረክ(LEARNING MANAGEMENT SYSTEM (LMS)) ግለሰቦች በፈለጉት ጊዜ በበይነ መረብ (online) አማካይነት የሚማሩበትን ሁኔታ የፈጠረ ሲሆን፣ በእያንዳንዱ ትምህርት (course) መጨረሻም ዕውቅናን (certification) የሚያስገኝ ነው፡፡

እኛ እምንሰራው

ሰዎች የኦንላይን ቢዝነስ
እንዲደራጁ መርዳት ነው

amAM